በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢራቅ ባንኮች ላይ በአሜሪካ የተጣለው እገዳ ተቃውሞን አስከተለ

አሜሪካ፣ 14 የኢራቅ ባንኮችን በጥቁር መዝገብ ውስጥ አሥፍራ በዶላር እንዳይገበያዩ ማገዷን ተከትሎ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ኢራቃውያን፣ በባግዳድ በሚገኘው ማዕከላዊ ባንክ ደጃፍ ላይ ተቃውሞ አድርገዋል፤ ባግዳድ፣ ኢራቅ
አሜሪካ፣ 14 የኢራቅ ባንኮችን በጥቁር መዝገብ ውስጥ አሥፍራ በዶላር እንዳይገበያዩ ማገዷን ተከትሎ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ኢራቃውያን፣ በባግዳድ በሚገኘው ማዕከላዊ ባንክ ደጃፍ ላይ ተቃውሞ አድርገዋል፤ ባግዳድ፣ ኢራቅ

አሜሪካ፣ 14 የኢራቅ ባንኮችን በጥቁር መዝገብ ውስጥ አሥፍራ በዶላር እንዳይገበያዩ ማገዷን ተከትሎ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ኢራቃውያን፣ በባግዳድ በሚገኘው ማዕከላዊ ባንክ ደጃፍ ላይ ተቃውሞ አድርገዋል።

በአሜሪካ የባንኮቹ እገዳ ምክንያት፣ የኢራቅ ዲናር ከዶላር ጋራ ያለው ምንዛሬ፣ ከ1ሺሕ470 ወደ 1ሺሕ570 አሻቅቧል።

ባለፈው የፈረንጆቹ ሐምሌ 19 ቀን፣ ባንኮቹ፣ በአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስትር እና ኒው ዮርክ በሚገኘው የፌዴራል ግምጃ ቤት መታገዳቸው ታውቋል። የርምጃው መነሻ፣ አጠራጣሪ በኾነ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ በማድረጋቸው እና ወደ ኢራቅ በመላካቸው ነው፤ ተብሏል።

የታገዱት 14ቱ ባንኮች ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ መንግሥት ለጉዳዩ መፍትሔ እንዲሰጠው ጠይቀው፣ ርምጃው፥ የዶላር ዋጋን ብቻ ሳይኾን፣ የውጪ ሙዓለ ነዋይ ላይም ተጽእኖ እንደሚያሳድር አስጠንቅቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG