በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራቅ ከፍተኛውን የአይሲስ መሪ ያዝኩ አለች


የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ አል ቃድሂሚ
የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ አል ቃድሂሚ

በኢራቅ የእስላማዊ መንግሥት አራማጁ ቡድን እና የረጅም ጊዜ የአልቃይዳ መሪ ከአገር ውጭ በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ አስታውቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ አል ቃድሂሚ ባወጡት የትዊት መልዕክታቸው ሳሚ ጄሰም በሚል ስም የሚታቀውና የእስላማዊ ቡድኑን ፋይናስን የሚመራ፣ ከአቡ ባክሪ አልባግዳዲ ቀጥሎ የአይ ኤስ ድርጅት ምክትል የነበረው ግለሰብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ግለሰቡ የታየዘው እጅግ አድካሚ በነበረ ምስጢራዊ ክትትልና የአገሩ ስም ባልተገለጸ ስፍራ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ አልባጋዳዲ እኤአ በ2019 ዩናይትድ ስቴትስ ባደረስቸው ድንገተኛ ጥቃት ሰሜን ምዕራብ ሶሪያው ስጥ መገደሉ ይታወቃል፡፡

XS
SM
MD
LG