በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራቅ ጦር ኃይሎች ሃዊያ ከተማን ከእሥላማዊ መንግሥት ነጠቁ


የኢራቅ ጦር ኃይሎች ሃዊያ ከተማን ከእሥላማዊ መንግሥት ቡድን ተዋጊዎች ነጥቀው መቆጣጠራቸውን የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይደር አል አባዲ አስታወቁ።

የኢራቅ ጦር ኃይሎች ሃዊያ ከተማን ከእሥላማዊ መንግሥት ቡድን ተዋጊዎች ነጥቀው መቆጣጠራቸውን የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይደር አል አባዲ አስታወቁ።

የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ከፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ሆነው ፓሪስ ላይ ዛሬ በሰጡት የድል ብሥራት መግለጫ “ድሉ የኢራቅ ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለምም ነው” ብለዋል።

ሃዊያ ከተማን ተቆጣጥሮ በነበረው የሁከትና የሽብሩ ቡድን ላይ ጥቃቱን ልክ የዛሬ ሁለት ሣምንት መስከረም 11 የከተፈቱት በዩናይትድ ስቴትስ የሚታገዘው የኢራቅ ጦርና ኢራን የምትደግፋቸው የሕዝባዊ ንቅናቄ ኃይሎች የሚባሉ ታጣቂ ቡድኖች መሆናቸው ተገልጿል።

“የኢራቅ ወታደሮች እጅግ ጨካኝና ቁርጠኛ ከሆነ ጠላት ጋር በጀግንነትና በባለሙያነት ተዋግተዋል” ሲሉ ኢራቅ የሚገኘው ጥምር ግብረ-ኃይል አዛዥ ሌተና ጄነራል ፖል ፈንክ አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

ለአሥራ አራት ቀናት በዘለቀው ውጊያ ከአንድ ሺህ በላይ ሽብርተኞች እጃቸውን መስጠታቸው ተነግሯል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG