ዋሺንግተን ዲሲ —
የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በባግዳድና በደቡባዊ ከተማዎች ላይ በከፈቱት ጥቃት ምክንያት ጋብ ብሎ የቆየው ታቃውሞ ዛሬ በአዲስ መልክ ማገርሸቱ ታውቛል።
ባግዳድ ያሉት የተቃውሞ ሰልፈኞቹ የተተኮሱባው እምባ አስማጪ ጋዝ ያያዙትን ቆርቅሮዎች መልስሰው በጸጥታ ሃይሎች ላይ እየወረወሩ መሆናቸው ተዘግቧል። 800 የሚሆኑ ተማሪዎች ረብሻ በታኝ ፖሊሶች በተጠቀሙት ሃይል ምክንያት ባስራ በተባለችው ደቡባዊት ከተማ ወደ ሚገኘው ሰፈር እንደተመለሱ ተገልጿል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ