በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራቅ ውስጥ በአሜሪካ በሚመራው ጥምር ጦር ሠፈር ላይ የድሮን ጥቃት ደረሰ


የኢራቅ ካርታ
የኢራቅ ካርታ

ጂሃዲስቶችን ለመፋለም በኢራቅ በሚገኘውና በአሜሪካ የሚመራው ጥምር ጦር ሰፈር ላይ በሁለት ድሮኖች ጥቃት መድረሱን የፀጥታ ባለስልጣናት ዛሬ አስታውቀዋል።

አንደኛው ድሮን ወታደራዊ ሠፈሩ ከመድረሱ በፊት ተመትቶ መውደቁንና፣ ሁለተኛውን በቅጥር ግቢው ውስጥ ቢወድቅም ምንም ጉዳት እንዳላደረሰ በጉዳዩ ላይ መናገር ፈቃድ ስላላገኙ ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠይቁ የፖሊስ ባላስልጣን ለኤ ኤፍ ፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

አንባር በተባለው አውራጃ ትላንት ምሽት የደረሰ ጥቃት የመጣው የአሜሪካ አጋር በሆነችው እስራኤልና በኢራን በሚደገፈው ሐማስ መካከል በጋዛ በሚካሄደው ጦርነት ምክንያት በቀጠናው ውጥረት ባየለበት ወቅት ነው።

ጥቃቱ የኢራቅን መንግስት “ለማሸማቀቅ” እንዲሁም በኢራቅ የሚገኘው ዓለም አቀፍ ቅንጅት የወደፊት ዕጣን በተመለከተ በመካሄድ ላይ ባለው ውይይት ላይ ጫና ለመፍጠር እንደሆነ፣ ጥቃት መድረሱን ያረጋገጡ አንድ በባግዳድ የሚገኙ ከፍተኛ ባለስልጣን አስታውቀዋል።

በኢራን የምደገፉ ቡድኖች ዓለም አቀፍ ቅንጅቱ ለቆ እንዲወጣ በመጠየቅ ላይ ናችው።

ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።

አሜሪካ በኢራቅ 2ሺሕ 500 እንዲሁም በሶሪያ 900 የሚሆኑ ከዓለም አቅፍ ጥምር ጦር ጋራ የተሰማሩ ወታደሮች አሏት፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG