ዋሺንግተን ዲሲ —
ከሥልጣናቸው እንዲሰናበቱ ያስወሰናቸው ምክንያት ምን እንደሆነ ሚኒስትሩ አልገለጹም። ፕሬዚዳንቱ ሃሰን ሩሃኒም ምላሽ አልሰጡበትም።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ግን ሃገራቸው የኢራኑ ሚኒስትር ሥራ መልቀቅ ውሳኔ መፅናት አለመፅናት እስኪለይ እየጠበቀች ናት ብለዋል።
ለማንኛውም እሳቸውና ሃሰን ሩሃኒ የምግብረ ብልሹ ሃይማኖታዊ ማፊያ ፊት ፊት የሚያስቀድማቸው ቢሆኑም ውሳኔውን ሁሉ የሚሰጡት ኻሚኒ መሆናቸውን እናውቃለን ያሉት ፖምፔዎ የኛ ፖሊሲ አልተቀየረም፣ አገዛዙ የጤናማ ሃገር ባህሪ መያዝና ህዝቡን ማክበር አለበት ብለዋል፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ