ዋና ከተማዪቱ ቴህራን ውስጥ የወጡ ስልፈኞች ዩናይትድ ስቴትስን የሚያወግዙ መፈክሮችን ሲያሰሙ የነበረ ሲሆን ፕሬዚዳንት ሃሰን ሮውሃኒ ባደረጉት ንግግር “ኢራናዊያን ለዋይት ሃውስ የቅርብ ጊዜ እርምጃ የሰጡት ምላሽ ነው፤ ኢራናዊያን ሌሎች በክብር እንዲያናግሩን እንፈልጋለን” ብለዋል።
“ኢራን በእሳት እየተጫውተች ነው” ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ቴህራን በቅርቡ ተምዘግዛጊ ሚሳይል በማስወንጨፏ ምክንያት ተጨማሪ ማዕቀቦችን ጥለውባታል።
በሌላ በኩል ደግሞ “ኢራን ግዙፏ የሽብር ፈጠራ አደራጅና አጋዥ ሃገር ነች” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ጄምስ ማቲስ ሰሞኑን ውንጀላ አሰምተዋል።
ኢራናዊያን ዛሬ ያከበሩት የአያቶላ አሊ ኾሜይኒ ደጋፊዎች በአሜሪካ ይደገፉ የነበሩትን ሻኽ ሬዛ ፓሕላቪን የጣሉበትን አብዮት ነው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ