የኢራን ደህንነት ኃይሎች ሰፔዲ ጎልያን የተባለችውን ተሟጋችና ጋዜጠኛ ትንናት ሀሙስ ከእስር ቤት በተለቀቀች ሰዓታት ውስጥ ወዲያውኑ መልሰው ማሰራቸው ተነገረ፡፡
ጎልያና የታሰረችው ከእስር ቤት እንደተቀለቀች የመንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ካሚኒን የሚያወግዝ መፈክር በማሰማቷ ነው ተብሏል፡፡
እኤአ በ2018 በኢራን የተነሳውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ዘግባለች በሚል የታሰረቸው የ28 ዓመቷ ጎሊያን ቴህራን ውስጥ አራት ዓመታት ከታሰረችበት እስር ቤት የተለቀቀችው ባላፈው ረቡዕ ረፋዱ ላይ እንደነበር ተገልጿል፡፡
ጎልያን ከእስር ቤት እንደተለቀቀች “አምባገነኑ ካሚኒ ወደ መሬት ጎትተን እንጥልሃለን!” በሚል ሁለት ጊዜ ደግሞ ያሰማችሁ መፈክር የታየበት የቪዲዮ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት መለቀቁ ተገልጿል፡፡
የኢራን መንግሥት ሴቶች በአደባባይ እንዲከናነቡ ካወጣው የአለባበስ ህግ በተቃራኒ ምንም ዓይነት ሻሽም ሆነ ስካርፍ ሳታደርግ መታየቷም ተጠቅሷል፡፡ ጎልያን፣ የታሰሩት ሌሎች ሴት ተሟጋችና የፖለቲካ እስረኞችም እንዲፈቱ መጠየቋንም የቪዲዮ ምስል እንደሚያሳይ ተገልጿል፡፡