በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስረኞችን ነፃ ለማውጣት አሜሪካ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ለኢራን እንዲለቀቅ ፈቀደች


የዩናይት ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የዩናይት ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

ከኢራን ጋራ የእስረኞች ልውውጥ እንዲደረግ የተስማማችው አሜሪካ፣ በተቀማጭ ገንዘብ ላይ ጥላ የነበረውን ማዕቀብ በጊዜያዊነት በማንሣት፣ ከደቡብ ኮሪያ እና ከኳታር ስድስት ቢሊዮን ዶላር እንዳስተላለፈች፣ ሮይተርስ ተመለከትኹት ያለውን የአሜሪካ መንግሥት ሰነድ ጠቅሶ ዘግቧል።

ስለ ገንዘቡ ቤዛ፣ በኢራን የተያዙ አምስት የአሜሪካ ዜጎች እንደሚለቀቁና በአሜሪካ የተያዙ አምስት ኢራናውያንም ነፃ እንደሚወጡ ታውቋል።

በኢራን ከተያዙት ውስጥ፣ ጥምር ዜግነት ያላቸው የአካባቢ ጥበቃ ባለሞያው ሞራድ ታህባዝ እና ነጋዴው ሲያማክ ናማዚ እንደሚገኙበት ተጠቁሟል።

ማዕቀቡን ለጊዜው ማንሣት፣ የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነትን ፍላጎት የጠበቀ እንደኾነ፣ ሚኒስትሩ አንተኒ ብሊንከን እንዳመኑበት፣ ከአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መ/ቤት የተገኘው ሰነድ አመልክቷል።

ማዕቀብ ተጥሎበት የነበረውና ለኢራን የተላከው ገንዘብ፣ ለአገሪቱ የሚሰጠው ጥቅም ውስን እንደኾነና “ለሰብአዊ ንግድ ልውውጥ” ብቻ እንደሚውል ተገልጿል።

የገንዘቡ እና የእስረኞች ልውውጡ፣ በሚቀጥለው ሳምንት ሊካሔድ እንደሚችልም ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG