በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራኑ የኒክሉየር ድርድርና የአሜሪካ ማዕቀብ


 የኢራን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሮሃኒ ከቀኝ በስተቀኝ የኢራን አቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ሀላፊ አሊ አክባር ሳሌሂ (በወቅቱ ሚያዝያ 10 ቀን 2021 (እ.ኤ.አ.) በኢራን ፕሬዝዳንት ጽ /ቤት የተለቀቀ ምስል)
የኢራን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሮሃኒ ከቀኝ በስተቀኝ የኢራን አቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ሀላፊ አሊ አክባር ሳሌሂ (በወቅቱ ሚያዝያ 10 ቀን 2021 (እ.ኤ.አ.) በኢራን ፕሬዝዳንት ጽ /ቤት የተለቀቀ ምስል)

ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን ጋር ወደሚደረገው የኒኩዩለሩ ስምምነት ንግግር በመመለሷ ስምምነቱን ውጤታማ ሆኖ በተሟላ መንገድ ተግባራዊ የሚደረግበትን መንገድ የመሻቱ ድርድር ቀጥሏል፡፡ ታዛቢዎች እንደሚሉት ኢራን በምትኩ ካሽመደመዳት የአሜሪካው ማዕቀብ ጨርሶ መገላገል የምትፈግል እንኳ ቢሆን፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው የኒኩለየር መስፋፋት በቸልታ ሊታይ የሚገባው ሳይሆን መፈታት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የቪኦኤ ዘጋቢ ዴል ጋቭላክ ከአማን እንደዘገበው ከሆነ፣ በክልሉ በስፋት ተሰራጭተው የሚገኙት በኢራን የሚደገፉ የሺያ ሚሊሺያዎች እና ሚሳኤሎች ጉዳይም እልባት ማግኘት ያለበት መሆኑን ተንታኞች ያሳስባሉ፡፡

ዴቪድ ሼንከር በዋሽንግተን ቅርብ ምስራቅ ፖሊሲ ተቋም ተመራማሪ ሲሆኑ በትራምፕ አስተዳደር ደግሞ የመካከለኛው ምስራቅ ፖሊሲ አማካሪ ነበሩ፡፡ እሳቸውና ሌሎቹ ታዛቢዎች እንደሚሉት ኢራን ከተጣሉባት ማዕቀቦች ለመገላገል እጅግ በጣም ትፈልጋለች፡፡ ወደ ኒዩክለር ስምምነቱ ከመመለስ በፊትም በቅድሚያ ሁሉም ማዕቀቦች እንዲነሱም ትጠይቃለች፡፡

ይሁን እንጂ ሼንከር፣ ድርድሩንም ሆነ የኢራንን እኩይ ባህርይና፣ በወኪሎችዋም አማካይነት፣ በክልሉ ከምታካሂደው ያልተገባ ድርጊት እንድትቆጠብ ለማድረግ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ይህን አጋጣሚ መጠቀም አለባት ይላሉ፡፡ እንዲህ ይላሉ

“ከማዕቀቦቹ በቂ የሆነው ክፍል ቢነሳ ለኢራናውያኑ በሌሎቹ ዋና ዋና ጉዳዮች እንዲነጋገሩ የማያስችላቸው ምንም ምክንያት አይኖርም፡፡ እነሱም ሚሣኤሎችንና መከካለኛውን ምስራቅ በማተራመስ ላይ የሚገኙትን በኢራን የሚደገፉ የሺያ ሚሊሺያዎችን የሚመለከቱ ናቸው፡፡ ከኢራቅ አንስቶ እስከየመን ከዚያም እስከ ሶሪያ ሊባኖስ ድረስ ኢራን የምታደርገው ነገር፣ ድርድሩን አስመልክቶ አሸናፊ ሆና ለመውጣት፣ በባይደን አስተዳደር ላይ የሚደረገው ግፊት እንዲጨምር ዘመቻ ማካሄድ ነው፡፡

የኢራኑ የኒክሉየር ድርድርና የአሜሪካ ማዕቀብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:40 0:00


ሼንከር አያይዘው፣ በቅርቡ ኢራቅ ውስጥ፣ በአሜሪካ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ላይ፣ የተቃጥቃውንም ሙከራ እና፣ እንዲሁም የመን ውስጥ በሚገኙ የሁቲ አማጻያን አማካይነት፣ ወደ ሳኡዴ አረብያ የሚደረገወን የድሮን ጥቃት ጠቅሰዋል፡፡

ምንም እንኳ፣ የባይደን አስተዳደር ሁቲዎችን ከተፈረጁበት የሽብረተኝነት ቡድን ዝርዝር ውስጥ፣ ነጻ ቢያወጣቸውም፣ የኢራን ፈጣን ጀልባዎች በባህረ ሰላጤ ያሉትን የአሜሪካ ባህር ኃይል መርከቦች መተናኮላቸውን ቀጥለዋል፡፡

ይሁን እንጂ፣ የዓለም አቀፉ ፋይናንሽናል ታይምስ ኤዲተር፣ ዴቪድ ጋርድነር፣ በአንድ የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ዓለም አቀፍ ተቋም መድረክ ላይ እንደተናገሩት፣ እሳቸው እየተመለከቱ ያሉት፣ በማእቀቡ የተሽመደመደችውን ደካማዋን ኢራንን ነው፡፡

በክልሉ እንደልቧ ማወክ አለመቻልዋንና፣ በአለፈው ዓመትም የወታደራዊ ስትራቴጅስት መኮንኗ፣ ጀኔራል ቃስም ሶሌማኒ፣ በአሜሪካ የአየር ኃይል ጥቃት የተገደሉባት መሆኑን ነው፡፡

ዴቪድ እንደሚሉት፣ ኢራቅ፣ ሶሪያና ሊባኖስ የወደቁ መንግሥታት እንጂ አቅም ያላቸው ኃይለኞች አይደሉም፡፡ ኢራን፣ ከሶሌማኒ ሞት በኋላ ሁኔታዎችን ለማስተካከል እየታገለች ነው፡፡ በሚሊሺ ና በሚሳኤሎች ብቻ ትክክለኛውን አቅምና ኃይለኝነት መገንባት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ማዕቀቦቹ እንዲነሱ መጣጣር እጅግ በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡

ስለተገደሉት የኢራን ጀኔራልም ዴቪድ እንዲህ ብለዋል

“የሶሌማኒ መገደል የተለያዩ ቡድኖችን ወደ አንድነት ለማጣምት ትልቅ እንቅፋት ፈጥሯል፡፡ ወታደራዊ ጀኔራል የነበሩት ሶሌማኒን የሚተካ አንድም ሰው አልተገኘም፡፡ እሳቸው አረብኛ ይናገራሉ፡፡ ከኩርዶች ጋር ብቻ ሳይሆን ከሱኒዎቹ የአረብ መሪዎችም ጋር የግ ንኙነት ድልድልይ ፈጥረው ነበር፡፡ የሳቸው ድንገተኛ ሞት በመዋቀሩ ደካማ መሆኑን አመልክቷል፡፡”

ይህም ሆኖ ግን፣ የለንደኑ ዓለም አቀፍ የስትራቴጂክ ጥናት ተቋም እንደሚለው፣ የቅርብ ጊዜ የሳታላይት ምስሎች እንደሚሳዩት፣ በደቡባዊ የኢራን ግዛት ውስጥ የተተከሉት ሰባት አዳዲስ ሚሳኤሎች፣ ለሳኡዲ አረብያና ባህሬን ውስጥ ለሚገኙ ወታደራዊ የአየር ኃይል ማረፊያዎች፣ ትልቅ አደጋ ደቅነዋል፡፡

ሌሎች በኢራን የሚደገፉ ሚሊሻዎችም፣ ኢራቅና ሶሪያን በሚያገናኙ ስትራቴጂክ አካባቢዎች፣ የእስላማዊ መንግሥት ታጣቂዎችን ሽንፈት ተከትለው ለመጠናከር እየሞከሩ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG