በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራንና የዩናይትድ ስቴትስ በኒዩክሌየር ስምምነትና ማዕቀቡ ድርድር አሁንም አልተግባቡም


ፎቶ ፋይል፦ ባለሥልጣናቱ በቪየና፣ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ ቬና ዴሴምበር 9/2021
ፎቶ ፋይል፦ ባለሥልጣናቱ በቪየና፣ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ ቬና ዴሴምበር 9/2021

ኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ እኤአ በ2015 የተደረሰበትን የኒዩክሊየር ስምምነት እንደገና ለማዳስ በሚደረገው ድርድር ላይ ወሳኝ በሆኑ ነጥቦች ለመስማማት ተቸግረዋል ተባለ፡፡

ሁለቱን የሚያግባባ ነገር በቶሎ መገኝቱም ጥያቄ እያስነሳ ነው ሲሉ ዲፕሎማቶች ተናገሩ፡፡

ስምንት ዙር ውይይት ከተካሄደ በኋላ የስምምነቱ ቁልፍና አስቸጋሪ ነጥቦች አሁንም በቦታው መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ኢራን ማዕቀቡ በምን ያህል መጠንና በምን ፍጥነት እንደሚነሳላት፣ እንዲሁም ተጨማሪ የቅጣት እምርጃዎች የማይወሰዱባት መሆኑን ለማረጋገጥ ለዩናይትድ ስቴትስ ዋስትና መስጠት፣ በኢራን የአውቶሚክ ግንባታው እንዴትና መች ወደ ነበረበት መመለስ እንደሚቻል የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

የስምምነቱ መሰረተ ሀሳብ ኢራን የኒዮክሊየር መሳሪያዎችን ግንባታ ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት መገደብን የሚጠይቅ ነው፡፡

ኤራን በበኩላ እንደዚያ ያለ ምኞት የሌላት መሆኑን በመግለጽ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተጣለባት ማዕቀብ በቶሎ እንዲነሳለት ትጠይቃለች፡፡

ይህንኑ መሰረት በማድረግ እኤአ በ2018 ተደርሶበት የነበረውን ስምምነት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢራንን በበቂ ሁኔታ የሚያስገድዳት አይደለም በሚል ውድቅ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡

XS
SM
MD
LG