በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶርያ በተቃዋሚዎች የተያዘ ቦታን የማስመለስ ዕቅድ ኢራን ደገፈች

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሐመድ ጃቫድ ዛሪፍ
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሐመድ ጃቫድ ዛሪፍ

ሶርያ የመጨረሻውን በተቃዋሚዎች ቁጥጥር ሥር ያለውን ቦታ ለማስመለስ ለያዘችው ዕቅድ ኢራን የድጋፍ ድምፅ እያሰማች ነው። በሰሜን ምስራቅ ሶርያ ያለው ዒድሊብ ክልል ከአሸባሪዎች ነፃ መሆን አለበት ማለትዋ ተገልጿል።

ሶርያ የመጨረሻውን በተቃዋሚዎች ቁጥጥር ሥር ያለውን ቦታ ለማስመለስ ለያዘችው ዕቅድ ኢራን የድጋፍ ድምፅ እያሰማች ነው። በሰሜን ምስራቅ ሶርያ ያለው ዒድሊብ ክልል ከአሸባሪዎች ነፃ መሆን አለበት ማለትዋ ተገልጿል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሐመድ ጃቫድ ዛሪፍ ከሶርያው አቻቸውና ከፕሬዚዳንት ባሻር አል አሳድ ጋር ተገናኝው ለመነጋገር ዛሬ ወደ ደማስቆ ሄደዋል። ዒድሊብ ወደ ሶርያ ህዝብ ቁጥጥር መመለስ ይኖርባታል። የመልሶ ግንባታ ተግባርና የሰደተኞች መመለስ መቀጠል አለበት ሲሉ ዛሪፍ መናገራቸውን የኢራን ሚድያ ጠቅሷል።

ሀገሪቱ ለሰባት ዓመታት ያህል ጦርነት ላይ ትገኛለች። የመንግሥት ደጋፊዎች፣ የአማፅያን ቡድኖች፣ የተለያዩ አካባቢዎችን የመቆጣጠር ፍላጎት ያላቸው ሚሊሻዎች በየፊናቸው ሲዋጉ ቆይተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG