በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን ውስጥ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ 103 ሰዎች ተገደሉ


በደረሱ ፍንዳታዎች የሞቱ ሰዎች አስከሬን አካባቢ ሰዎች ተሰባስበው ከርማን፣ ኢራን፤ እ አ አ ጥር 3/2024
በደረሱ ፍንዳታዎች የሞቱ ሰዎች አስከሬን አካባቢ ሰዎች ተሰባስበው ከርማን፣ ኢራን፤ እ አ አ ጥር 3/2024

ኢራን እ.ኤ.አ. በ2020 በአሜሪካ በተፈጸመ የአየር ጥቃት የተገደሉትን ታዋቂ ኢራናዊ ጄኔራል ለመዘከር በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ዛሬ በደረሱ ፍንዳታዎች በትንሹ 103 ሰዎች ሲሞቱ 141 ቆስለዋል።

የኢራን መንግሥት ዜና ማሰራጫ ጥቃቱን “የሽብር” ጥቃት ብሎታል፡፡

የትናንቶቹ ፍንዳታዎች የደረሱት የአብዮታዊ ዘቡ መሪ የነበሩት ጄኔራል ቃሴም ሱሌማኒ የተገደሉበት አራተኛ ዓመት በሚዘከርበት ዝግጅት ላይ ነበር።

የጀመሪያው ፍንዳታ የተሰማው ከዋና ከተማዪቱ ቴህራን በስተደቡብ ምስራቅ 820 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ከርማን ውስጥ በሚገኘው የሱሌማኒ መቃብር አቅራቢያ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ከ15 ደቂቃዎች በኋላ የደረሰው ሁለተኛው ፍንዳታ ለአደጋው ምላሽ ለመስጠት የሚሰማራውን ጦር እና የአደጋ ጊዜ እና ነፍስ አድን ሠራተኞችን ኢላማ ያደረገ እንደነበር ተገልጿል፡፡

የከርማን ምክትል ገዥ ራህማን ጃላሊ ያለምንም ማብራሪያ ጥቃቱን "የሽብር" ብለውታል።

ኢራን ከጥቃቱ ጀርባ ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ጠላቶች እንዳሏት የተነገረ ሲሆን በግዞት የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች፣ ታጣቂ ድርጅቶችን እና የመንግሥት ተዋናዮችን ይጨምራል፡፡

ኢራን ሐማስንና የሊባኖስ የሺዓ ሚሊሻ ሂዝቦላህን፣ እንዲሁም የየመንን እና ሁቲ አማፂያንን ትደግፋለች።

ለጥቃቱ እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ የለም፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG