በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን በሰላም ኖቤል አሸናፊ ሎሬት ላይ ተጨማሪ የስድስት ወራት እስራት ፈረደች


ኢራናዪቷ የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ሎሬት ናርጀስ ሞሃመዲ
ኢራናዪቷ የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ሎሬት ናርጀስ ሞሃመዲ

ለኢራናዪቷ የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ሎሬት ናርጀስ ሞሃመዲ የሚሟገተው ቡድን የኢራን ባለሥልጣናት ተሸላሚዋን ተጨማሪ የስድስት ወር እስራት የፈረደቧቸው መሆኑን አስታወቀ፡፡

“ናርጀስ ትፈታ” በሚል የተሰባበው ቡድን ትላንት ሐሙስ ባወጣው መግለጫ፣ የሰላም ኖቤል ተሸላሚዋ ናርጀስ ሞሃመዲ ትእዛዝ በመቃወም እና ባለማክበር ክስ፣ እኤአ ጥቅምት19 ተጨማሪ የ6 ወራት እስራት ተፈርዶባቸዋል ብሏል፡፡

የመብት ተሟጋቿ ሞሃመዲ ላይ ተጨማሪው ክስ የተመሰረተባቸው “ሴቶች በሚታሰሩበት የኢቫን እስር ቤት የሞት ቅጣት የተፈመጸባቸውን ሌላኛዋን የፖለቲካ እስረኛ ቅጣት በመቃወማቸው ነው” ሲል የቡድኑ መግለጫ አክልሏል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2023 የኖቤል የሰላም ሽልማትን ያገኙት ናርጂስ ሞሃመዲ፣ ይህንን ክብር ከተቀበሉ ሁለት ኢራናውያን ሴቶች አንዷ ሲሆኑ ሌላኛዋ እ.ኤ.አ በ2003 ያሸነፉት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቿ ሺሪን ኢባዲ ናቸው።

የ52 ዓመቷ ናርጂስ በኢራናውያን ባለሥልጣናት በርካታ እስሮችን ያስተናገዱና ለዓመታት ታስረው የቆዩ ቢሆኑም ተሟጋችነቱን ቀጥለውበታል።

ሞሃምዲ የታሰሩት የፖለቲካ እስረኞች እና ከምዕራቡ ዓለም ጋር የተሳሰረ ግንኙት ያላቸው ሰዎች በሚታሰሩበት መጥፎ ዝና ባለው የኢቫን እስር ቤት ውስጥ ነው፡፡

አዲሱ የ6 ወራት እስራት የተፈረደባቸው፣ ባላፈው ጥር የተጨመረባቸውን ሌላ የ15 ወራት እስራት ጨምሮ የተፈረደባቸውን የ30 ወራት እስራት እየተወጡ ባላበት ወቅት መሆኑን የአሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG