በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ኢራን ለሩሲያ ድሮን በማቅረቧ የተመድን ውሳኔ ተላልፋለች” አሜሪካ


ፎቶ ፋይል፦ በሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት በተፈፀመ ፍንዳታ፣ በአውራ ጎዳናዎች ላይ የሚታይ ፍርስራሽ፤ ኪየቭ፣ ዩክሬን እአአ 10/17/2022.
ፎቶ ፋይል፦ በሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት በተፈፀመ ፍንዳታ፣ በአውራ ጎዳናዎች ላይ የሚታይ ፍርስራሽ፤ ኪየቭ፣ ዩክሬን እአአ 10/17/2022.

የሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለሩሲያ በማቅረቧ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ም/ቤት ውሳኔን ተላልፋለች ስትል ዩናይትድ ስቴትስ ትናንት ኢራንን ከሰሰች።

“የፈረንሣይና የእንግሊዝ አጋሮቻችን ያላቸውን ግምገማ አጋርተውናል። ኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለሩሲያ በማቅረቧ የፀጥታው ም/ቤትን ውሳኔ ቁጥር 2231 የሚጥስ ሆኖ አግኝተውታል፤ እኛም በዚህ እንስማማለን” ሲሉ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ቃል-አቀባይ ቬዳንት ፓቴል ለሪፖርተሮች ተናግረዋል፣ ሲል የቪኦኤ የፐርሺያ ቋንቋ አገልግሎት ዘግቧል።

ኢራን የኑዮክሌር ፕሮግራሟን አንድትገታና በምትኩ የተጣለባት ማዕቀብ እንዲላላ ሲል የጸጥታው ም/ቤት በእአአ 2015 ወስኖ ነበር።

“ከኢራን ለሩሲያ የተሰጡትና፣ ሩሲያ ዩክሬን ላይ የተጠቀመቻቸው ሰው አልባ አውሮፕላኖች በውሳኔ ቁጥር 2231 የተካተቱና ማዕቀብ የተጣለባቸው እንደሆኑ እናምናለን” ሲሉ አክለዋል የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ምክትል ቃል-አቀባዩ።

ላለፉት ጥቂት ሳምንታት ኢራን ሠር በሆኑት ሻሂድ-136 ድሮኖች ከተሞቼን ደብድባለች ስትል ዩክሬን በተደጋጋሚ ማስታወቋ ይታወሳል።ኢራን ሩሲያን የሰው አልባ አውሮፕላኖች በማስታጠቅ የሚቀርብባትን ውንጀላ ክሱን ታስተባብላለች።

“ኢራንያውያኑ ዩክሬንን ለማጥቃት ጥቅም ላይ የዋሉትን መሳርያዎች የማቅረባቸው ጉዳይ ላይ ይዋሻሉ” ሲሉ የዋይት ሃውሷ የፕረስ ፀሃፊ ካሪን ዣን ፒየር ትናንት ለዜና ሰዎች ተናግረዋል።

የፕረስ ፀሃፊዋ አክለውም፣ “ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያና በኢራን የሚካሄደው የጦር መሳሪያ ንግድ ላይ ያለውን ማዕቀብ ተግባራዊ ታደርጋለች። ኢራንም ለሩሲያ መሣሪያ እንዳትሸጥ መንገዱን ከባድ ታደርግባታለች” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG