በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ በኢራን ላይ የተጣለው የምጣኔ ኃብት ማዕቀብ ከፍ እናደርገዋለን አሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በኢራን ላይ የተጣለውን የምጣኔ ኃብት ማዕቀብ በቅርቡ በጣም ከፍ እናደርገዋለን ሲሉ ተናገሩ።

ዩናይትድ ስቴትስ ቴህራንን የኒውክሊየር መርኃ ግብሩዋን ለመገደብ የታለመውን ዓለምቀፉን ስምምነት የምትጥሰው በኒውክሊየር አማካይነት የምትፈልገውን ለማስፈፀም ነው ስትል ዩናይትድ ስቴትስ ወንጅላለች።

ኢራን በስምምነቱ ከተፈቀደላት በላይ ዩሬንየም ማዳበሩዋን እና ማከማቸቷን አምናለች። ፕሬዚዳንት ትረምፕ ዩናይትድ ስቴትስን ባለፈው ዓመት ከውሉ አስወጥቷታል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ኢራን ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ጥሳ በድብቅ ዩሬንየም ስታበለፅግ ቆይታለች ሲሉ አምነዋል። ውሉን ፕሬዚዳንቱ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃን ኬሪ እና የኦባማ አስተዳደር ለኢራን አንድ መቶ ሃምሳ ቢሊዮን ዶላር ሊመልሱላት የተስማሙበት መጥፎ ውል ሲሉ ጠርተውታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG