በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ተቃውሞው የአሜሪካና የእስራኤል እጅ አለበት” እያቶላ


ኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ካኻመኒ
ኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ካኻመኒ

በኢራን የአንዲት ወጣት በፖሊስ እጅ ሳለች መሞትን ተከትሎ በሀገሪቱ የተቀጣጠለው ተቃውሞ “የተራ ኢራናውያን” ተግባር ሳይሆን የዩናይትድ ስቴትስ እና የእስራኤል ዕቅድ ነው ሲሉ የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ካኻመኒ ሁለቱን ሀገሮች ወንጅለዋል።

ሦሰተኛ ሳምንቱን የያዘው ተቃውሞ ከፀጥታ ኃይሎች ብርቱ መልስ ገጥሞታል። መንግሥት 14 ሞተው 1ሺህ 500 የሚሆኑት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ሲገልጽ፤ የመብት ተሟጋቾች ግን ቢያንስ 130 መሞታቸውንና በሺህዎች የሚቆጥሩ እንደተያዙ ይገልጻሉ ሲል አሶስዬትድ ፕረስ ዘግቧል።

የ22 ዓመቷ ወጣት ማሻ አሚኒ መሞት “አሳዛኝ ክስተት” ነው ያሉት ካኻመኒ በሁኔታው ልባቸው እንደተሰበረ ተናግረዋል።

የኢራን የሥነ ምግባር አስከባሪ ፖሊስ “አለባበስሽ ሥርዓትን የተከተለ አይደለም” በሚል በቁጥጥር ስር ካዋላት በኋላ፣ ራሷን በመሳቷ ወደ ሆስፒታል ተወስዳ ነበር። ከሦስት ቀናት በኋላም ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል።

መንግስት ወጣቷ በልብ ድካም እንደሞተች ይናገራል። ወላጆቿ ግን ያንን ውድቅ በማድረግ፣ ማሻ ምንም ዓይነት የልብ ችግር እንደሌለባት ተናግረው፣ በተፈጸመባት በድብደባ እንደሞተች ይገልጻሉ። ለዚህም ሃላፊነት እንዲወሰድ ይጠይቃሉ።

ኢራን በተቃዋሚዎች ላይ የምታደርገውን የሃይል ምላሽ በማውገዝ በበርካታ ሀገራት በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ትናንት ዕሁድ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።

“ማሻ አሁን በህይወት የሌለችው፣ ጨካኙ ሥርዓት ህይወቷን ስለነጠቀ ነው፤ ይህም የሆነው የምትለብሰውንና ያማትለብሰውን ልብስ የመምረጥ ውሳኔንን የራሷ በማድረጓ ነው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር አንተኒ ብሊንከን በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG