በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የየመን አማፅያን ሳውዲ አረብያን ለማጥቃት ከኢራን ያገኟቸውን መሣርያዎች ተጠቅመዋል - ዩናይትድ ስቴትስ


የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሐማድ ጃቫድ ዛሪፍ
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሐማድ ጃቫድ ዛሪፍ

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሐማድ ጃቫድ ዛሪፍ ኢራን መሰረት የሌለው ያሉትን የዩናይትድ ስቴትስ ክስን ትከታተላለች ብለዋል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሐማድ ጃቫድ ዛሪፍ ኢራን መሰረት የሌለው ያሉትን የዩናይትድ ስቴትስ ክስን ትከታተላለች ብለዋል።

የመን ያሉ አማፅያን ሳውዲ አረብያን ለማጥቃት ከኢራን ያገኟቸውን መሣርያዎች ተጠቅመዋል ስትል ዩናይትድ ስቴትስ መክሰስዋን ነው የኢራኑ ባለስልጣን የገለፁት።

የዩናይትድ ስቴትስ ርምጃዎች ተንኳሾች ናቸው፤ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲህ ዓይነት ክስ የምትሰነዝረው በንፁሃን የመናውያን ላይ ለሚካሄደው ድብደባ ያላትን ድጋፍ ለመሸፋፈን ነው ሲሉ ዛሪፍ መናገራቸውን የመንግሥቱ እስላማዊ ሪፖብሊክ የዜና አገልግሎት ጠቅሷል።

ኢራን የየመንን መዲና ከአራት ዓመታት በፊት የተቆጣጠሩትን ሁቲ አማፅያንን ትደግፋለች።

ይሁንና መሣርያ ታቀረብላቸዋለች የሚለውን ክስ ታስተባብላለች። ዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ በሳውዲ አረብያ የሚመራውን ጥምረት ትደግፋለች። ጥምረቱ ዓለምቀፍ እውቅና ያገኙትን ፕሬዚዳንት አብዱ ራቡ ማንሱር ሐዲን በመደገፍ ለሦስት ዓመታት ያህል ሁቲ አማፅያንን ሲዋጋ ቆይቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG