በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራን መንፈሳዊ መሪና አጋር የሚሊሺያ ተወካዮች ለራይሲ ፀሎት አደረጉ


የኢራን መንፈሳዊ መሪና አጋር የሚሊሺያ ተወካዮች ለራይሲ ፀሎት አደረጉ
የኢራን መንፈሳዊ መሪና አጋር የሚሊሺያ ተወካዮች ለራይሲ ፀሎት አደረጉ

የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒ እና የሃገሪቱ አጋር ሚሊሺያ ተወካዮች ባለፈው እሁድ በሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸውን ላጡት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት እንዲሁም ለውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩና ለሌሎችም ስድስት ባለሥልጣናት ፀሎት አድርገዋል።

በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች በቴህራን አውራ ጎዳናዎች ላይ ዛሬ ረቡዕ አስከሬኖችን አጅበው ሲጓዙ ተስተውለዋል። አብዛኞቹ ከመዲናዋ ቴህራን ውጪ ከሚገኙ ከተሞች መምጣታቸውን ተናግረዋል።

ለፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ለተካሄደው ሥነ ሥርዓት የወጣው ሕዝብ ቁጥር፣ ከአራት ዓመታት በፊት በባግዳድ በአሜሪካ የድሮን ጥቃት ለተገደሉ የአብዮታዊ ዘብ ጄነራል ቃሲም ሱሊማኒ ተፈጽሞ ለነበረው ሥነ ስርዓት ከወጣው ያነሰ እንደሆነ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

የኢብራሂም ራይሲ እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሆሴን አሚራብዶላሂያን ህልፈት የመጣው ኢራን በውስጥም ሆነ በውጪ የፖለቲካ ቀውስ በገጠማት ወቅት ነው።

የ63 ዓመቱ ኢብራሂም ራይሲ፣ የ 85 ዓመቱን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒን ይተካሉ ተብለው ይጠበቁ ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG