በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕን ለመግደል አሲራለች መባሉን ኢራን ውድቅ አደረገች


ፎቶ ፋይል፦ የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ የነበሩት ቃስም ሶሊማኒ
ፎቶ ፋይል፦ የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ የነበሩት ቃስም ሶሊማኒ

ኢራን የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕን ለመግደል ሴራ ጠንስሳለች ሲል አንድ የአሜሪካ ሚዲያ ያቀረበውን ዘገባ “የክፋት” ስትል በመግለጽ ሃገሪቱ ውድቅ አድርጋለች፡፡

ኢራን ዶናልድ ትረምፕን ለመግደል ማሴሯን የሚያሳይ የደህንነት መረጃ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ከሳምንታት በፊት እንደደረሳቸውና ይህም ለትረምፕ የሚደረገው ጥበቃ እንዲጠናከር ማድረጉን ሲ ኤን ኤን ትላንት ማክሰኞ ዘግቦ ነበር። ሌሎች የዜና አውታሮችም በጉዳዩ ላይ ዘገበው ነበር።

ኢራን ዛሬ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሚገኘው ልዑኳ በኩል በሰጠችው ምላሽ፣ “በማስረጃ ያልተረጋገጠ” እና “የክፋት” ስትል ዘገባውን አጣጥላለች።

ከሁለት ዓመታት በፊት የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ የነበሩት ቃስም ሶሊማኒ ኢራቅ ዋስጥ በድሮን ጥቃት ከተገደሉ ወዲህ፣ ከኢራን በኩል በዶንላድ ትረምፕ ላይ የሚሰነዘሩ ዛቻዎችን ሲከታተል እንደነበር የአሜሪካው ብሔራዊ የፀጥታ ም/ቤት አስታውቋል።

ባለፈው ቅዳሜ በዶናልድ ትረም ላይ በተፈፀመው የግድያ ሙከራ ሴራ ውስጥ እንዳለችበት የሚነገረውን በጥብቅ እንደምትቃወም የሃገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናሰር ካናኒ አስታውቀዋል።

ነገር ግን ትረምፕ በጀኔራል ቃሰም ሶሊማኒ ግድያ ላይ ነበራቸው ላሉትና ቀጥተኛ ተሳትፎ ብለው በገልጹት ምክንያት ኢራን ክስ ለመክፈት ቁርጠኛ እንደሆነች ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል። ሶሊማኒ የአብዮታዊ ዘቡን የውጪ ዘመቻዎች በሃፊነት ይመሩ ነበር።

ሶሊማኒ ከባግዳድ አየር ማረፊያ ወጣ ብሎ ባለ ሥፍራ በነበሩበት ወቅት በድሮን ጥቃት እንዲገደሉ ትርምፕ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG