በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት መንግሥታት ዋናው የኒዩክሌር ተቆጣጣሪ ወደ ኢራን አመሩ


የተባበሩት መንግስታት የኒዩክሌር ቁጥጥር ተቋም ኃላፊ ራፋኤል ግሮሲ ከኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁሴን አሚራ አብዶላሂ
የተባበሩት መንግስታት የኒዩክሌር ቁጥጥር ተቋም ኃላፊ ራፋኤል ግሮሲ ከኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁሴን አሚራ አብዶላሂ

የተባበሩት መንግስታት የኒዩክሌር ቁጥጥር ተቋም ኃላፊ ራፋኤል ግሮሲ እየተፋጠነ ባለው የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ የኒውክሊየር መርሃ ግብር ላይ ተቋማቸው የሚያደርገውን ቁጥጥር ለማሻሻል ዛሬ ሰኞ ወደ ኢራን በርረዋል።

ግሮሲ “ኢራን ፍላጎቱ ካላት በርካታ ኒዩክሌር ቦምቦችን ለመሥራት የሚበቃት የበለጸገ ዩራኒየም አከማችታለች” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የኢራን ባለስልጣናት የአቶሚክ መሣሪዎችን በመስራቱ ልንገፋበት እንችል ይሆናል በማለት ዝተዋል።

የሻሂድ በሄሽቲ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር እና የኑክሊየር ፊዚክስ ባለሙያ የሆኑት ማህሙድ ሬዛ አጋሚሪ "ለእኛ የአቶሚክ ቦምብ ካለመስራት መስራቱ ይቀለናል” ብለዋል።

ግሮሲ የኢራን የኒዩክሌር ማብላያ ለሚስጥር ማበልጸጊያው እየዋለው ይሁን አይሁን ተቋማቸው ማረጋገጫ መስጠት እንደማይችል አምነዋል፡፡

ባለፈው ወር ለስካይ ኒውስ በሰጡት ቃል ኢራን ውስጥ “ያለን የምርመራ ደረጃ በሚገባው ደረጃ ላይ አይደለም” ሲሉ ግሮሲ አክለዋል፡፡

ግሮሲ ዛሬ ከኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁሴን አሚራ አብዶላሂ ጋር እንደሚገናኙ የኢራን መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል ።

“ግሮሲ ያላቸው አቅም ውስን ነው” ያሉት ተንታኞች እና ዲፕሎማቶች ያሏቸው ከባዶ ተስፋዎች መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል” ብለዋል፡፡

ቴህራን ባለፈው ሚያዝያ እስራኤል ላይ ታይቶ የማይታወቅ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሚሳይሎች ጥቃት አድርሰሳለች።

ጥቃቱ የተፈጸመው እስራኤል በሶሪያ በሚገኝ የኢራን ቆንስላ ህንፃ ላይ ሳትፈጸም አልቀረችም ተብሎ የተነገረውንና ሁለት የኢራን ጄኔራሎችን እና ሌሎችንም የተገደሉበትን ጥቃት ተከትሎ ነው፡፡

የእስራኤል የኒዩክሊየር ፕሮግራም ኢራንን ጥቃት ከመሰንዘር እንድትቆጠብ አላደረገም። ኢራን ከፍተኛ የሆነ ጥቃት ከተፈጸመባት ቦምቡን የመሥራቱን ጉዳይ ራሷ ልትገፋበት እንደምትችል ባለሙያዎች ጠቁመዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG