በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራን የኑክሌር ፕሮግራም


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የኢራንን የኑክሌር ፕሮግራም ለመገደብ ሲባል እአአ በ2015 ሥምምነት ከፈረሙት ሀገሮች የተጣለባትን ማዕቀብ ለማንሳት የሚያስችል ዕርዳታ ካላገኘች በስተቀር ኢራን ዩራንየሙን ከፍ ባለ ደረጃ ማዳበር ትጀምራለች ሲሉ የኢራን ፕሬዚዳንት ሐሰን ሩሃኒ ዛሬ ተናግረዋል።

ኃያላን ሀገሮች ከኢራን ጋር ሥምምነት ያደረጉት ኢራን ኑክሌር መሳራያ ለመስራት እየሞከረች ነው የሚለውን ሥጋት ለማርገብ ነበር። ሥምምነቱ ኢራን ዩርንያሙን ከ3.67 ከመቶ በላይ እንዳታዳብር ያግዳል፤ ልታከማች የምትቸለውም 300 ኪ.ግ ብቻ እንደሚሆን ሥምምነቱ ያዛል።

ሩሃኒ አያይዘውም ኢራን ከእሁድ አንስታ ከ3.67 ከመቶው ገደብ አልፋ የፈለግነውን ያህል መጠን ለማዳበር ተዘጋጅታ ነበር ብለዋል። የአራክ የከባድ ወሃ አንቀሳቃሽ ውጥን መገንባቱን ለመቀጠልም ቃል ገብተዋል። ኢራን እአአ በ2015 ከኃያላን ሀገሮቹ ጋር ሥምምነት በፈረመችበት ወቅት ውጥኑን ለመዝጋት ተስማምታ ነበር።

ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ዓመት ከሥምምነቱ ወጥታ በኢራን ላይ በርካታ ሌሎች ማዕቀቦችን በመጣልዋ ኢራን የአውሮፓን ዕርዳታ ለማግኘት ስትሞክር ቆይታለች። ዩናይትድ ስቴትስ የጣለችባት ማዕቀብ ቁልፍ የሆነውን የነዳጅ ዘይት ዘርፏንም ያካትታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG