በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በ2015ቱ የኢራን የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ሥምምነት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ


የዓለም ኃያላን ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ኢራን፣ ቪዬና ውስጥ በዛሬው ቀን ተገናኘው፣ በ2015ቱ የኢራን የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ሥምምነት ዙሪያ መወያየታቸው ተገለፀ።

ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ዓመት ከሥምምነቱ ከወጣች ወዲህ፣ ውሉን በፈረሙ ሀገሮች መካከል የሚካሄደው የአሁኑ ውይይት፣ ሥምምነቱን በዘላቂነት ለማቆየት፣ የአሁኑ የመጨረሻ ዕድል መሆኑን፣ ኢራን አስታውቃለች።

ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ ባለፈው ዓመት በጣለችው ማዕቀብ የተነሳ፣ ኢራን ዩራኒዬም ለማበልጸግ በሥምምነቱ የተፈቀደላትን መጠን ለማለፍ እያስፈራራች መሆኗም ታውቋል። እስካሁን ግን በሥምምነቱ የተወሰነውን ገደብ እንዳላለፈች ነው አንድ ባለሥልጣኗ ያመለከቱት።

የአውሮፓ ሀገሮችም ኢራን ሥምምነቱን እንድታከብር እያሳበቡ መሆናቸው ተሰምቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ መካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ውጥረት ማየሉ ተሰምቷል። መነሾው፣ ዩናይትድ ስቴትስ ቀደም ብላ ከላከቻቸው ብዙ ሺህ ወታደሮች በተጨማሪ፣ ሌሎች የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦችንና ወታደሮችን ወደ ክልሉ ማሰማራቷ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ ምክንያቷን ስትገልጽ፣ ኢራን የምታሰማውን ዛቻ ታነሳለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG