በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተገደሉት የኢራን ሳይንቲስት ሽኝት


ኢራን ባለፈው ዓርብ የተገደሉባትን የኒኩሌር ሳይንቲስቷን ሞህሴን ፋኽሪዛዴህን አስከሬን የቀብር ሥርዓት
ኢራን ባለፈው ዓርብ የተገደሉባትን የኒኩሌር ሳይንቲስቷን ሞህሴን ፋኽሪዛዴህን አስከሬን የቀብር ሥርዓት

ኢራን ባለፈው ዓርብ የተገደሉባትን የኒኩሌር ሳይንቲስቷን ሞህሴን ፋኽሪዛዴህን አስከሬን የቀብር ሥርዓት ዛሬ አከናውናለች።

ለግድያው አፀፋ እንደሚሰጡ የኢራን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በመከላከያ ሚኒስቴሩ ውስጥ በተከናወነው የሳይንቲስቱ አስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ የተናገሩት የኢራን የመከላከያ ሚኒስትር አሚር ሃታሚ “ግድያው ኢራናዊያንን ወደ ጠነከረ ህብረትና ቁርጠኛነት” እንደሚወስዳቸው ተናግረው ሃገራቸው ሥራዋን “በተፋጠነ ሁኔታና በበለጠ ኃይል” እንደምትቀጥል አስታውቀዋል።

የፋኽሪዛዴህ ገዳዮች ተኩስ ተኩስ የከፈቱባቸው አብሳርድ በምትባል የገጠር ቀበሌ አቅራቢያ በመኪናቸው እየተጓዙ ሳሉ እንደነበር ተዘግቧል።

ኢራን ለግድያው እሥራኤልን በተጠያቂነት የወነጀለች ሲሆን እሥራኤል ግን ክሡን አስተባብላለች።

ከግድያው በኋላ የኢራን ፓርላማ የዓለምአቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ተቋም የሚያካሂደውን ፍተሻ እንዲያቋርጥ ሊያደርግ በሚችል የህግ ረቂቅ ላይ መምከር መጀመሩ ተገልጿል።

ኢራን ኒኩሌር የጦር መሣሪያ እንዳትሠራ የሚያግዳትና በምላሹም ማዕቀቦች እንዲነሱላት በኢራንና በሌላ ወገን ደግሞ በስድስት ኃያላን መንግሥታት መካከል የዛሬ አምስት ዓመት ተፈርሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ ወጡበት ስምምነት ከሁለት ወራት ባነሰ ጊዜ ዋይት ሃውስ የሚገባው የተመራጩ የባይደን አስተዳደር የመመለስ ዕቅድ እንዳለው ይታወቃል።

XS
SM
MD
LG