በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን ለድሮን ጥቃቱ እስራኤልን ተጠያቂ አደረገች


ኢራን ለድሮን ጥቃቱ እስራኤልን ተጠያቂ አደረገች
ኢራን ለድሮን ጥቃቱ እስራኤልን ተጠያቂ አደረገች

ኢራን ባላፈው ቅዳሜ፣ በአገሪቱ ኢስፋሃን ከተማ ማዕከላዊ ስፍራ ለደረሰው የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት፣ እስራኤልን ተጠያቂ አደረገች፡፡

በተባበሩት መንግሥታት የኢራን ልኡክ ድረ ገጽ ላይ የተለጠፈው ደብዳቤ በቅድም ምርመራ የተገኙ ፍንጮች እንደሚያሳዩት “እስራኤል ለዚህ ጠብ አጫሪነት ሙከራ ተጠያቂ ነች” ብሏል፡፡

ደብዳቤው ዝርዝር ማሰረጃዎችን አላከተተም፡፡

ኢራን ወታደራዊ ተቋሙ የሚገኝበትን ህንጻ ኢላማ በማድረግ ጥቃት የፈጸሙት ድሮኖች ሦስት ሲሆኑ፣ ሁለቱ ተመተው ውድቀዋል ብላለች፡፡

የኢራን መከላከያ ሚኒስቴር ጥቃቱ በህንጻው ላይ መጠነኛ ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል፡፡

እስራኤል ከኢራን የኒውክለር መርሃ ግብር ጋር የተገናኙ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ በርካታ ጥቃቶችን እንደምታካሂድ፣ ከአሶስዬትድ ፕሬስ እና አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የተገኙ ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG