በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራን መንግሥት በወሰዳቸው ርምጃዎች የተቆጡ በፕሬዝዳንታዊው ምርጫ እንደማይሳተፉ ገለጹ


የኢራን የኒውክሌር ተደራዳሪ ሰኢድ ጃሊሊ በቴህራን፣ ኢራን እአአ ሰኔ 30/2024
የኢራን የኒውክሌር ተደራዳሪ ሰኢድ ጃሊሊ በቴህራን፣ ኢራን እአአ ሰኔ 30/2024

በመጪው አርብ በሚካሄደው የኢራን ሁለተኛ ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቀደም ሲል መንግሥቱ በወሰዳቸው ርምጃዎች ቅር የተሰኙ መራጮች ድምጻቸውን እንደማይሰጡ ተናገሩ።

ውሳኔው በቡድን የተወሰደ የአድማ ርምጃ አካል ሳይሆን፤ በተናጠል በግል ያደረጉት መሆኑንም በምርጫው እንደማይሳተፉ ለአሶሽዬትድ ፕሬስ የተናገሩ አስተያየት ሰጪዎች አመልክተዋል።

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1979 ከተካሄደው የኢራን እስላማዊ አብዮት ወዲህ በዚያች አገር የሁለተኛ ዙር ምርጫ ሲካሄድ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው። ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ድምጽ የሰጠው ሕዝብ መምረጥ ከሚችለው ከ40 በመቶ በታች መሆኑም ታውቋል።

በፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ከረር ባለ አቋማቸው የሚታወቁት የቀድሞው የሃገሪቱ የኒውክሌር ተደራዳሪ ሰኢድ ጃሊሊ እምብዛም እውቅና የሌላቸውን የለውጥ አራማጁን ማሱድ ፔዜሽኪያን’ን ይገጥማሉ። ማሱድ አሸንፈው የፕሬዝዳንትነቱን መንበር የመቆናጠጥ ዕድል እንዲቀናቸው ሰፊ የመራጭ ተሳትፎ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ለተቃውሞ በወጡ ዜጎች ላይ የተወሰዱትን እና የንጹሃን ደም የፈሰሰባቸውን ርምጃዎች፤ እንዲሁም እስካሁን ከታየው ሁሉ እጅግ ዝቅተኛው ደረጃ መድረሱ የተነገረለት የሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት ይዞታ የከሰተውን ሁኔታ ተከትሎ ብርቱ የሕዝብ ቁጣ መንገሱን አሶሽዬትድ ፕሬስ በዘገባው ጠቁሟል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG