በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢራን ሴት ተማሪዎችን በመመረዝ የተጠረጠሩ ተያዙ


በኢራን ሴት ተማሪዎችን በመመረዝ የተጠረጠሩ ተያዙ
በኢራን ሴት ተማሪዎችን በመመረዝ የተጠረጠሩ ተያዙ

ከሴት ተማሪዎች መመረዝ ጋር ግኑኝነት አላቸው ያለቻቸውን በርካታ ሰዎች መያዟን ኢራን አስታውቃለች፡፡ ግለሰቦቹ በውጪ ከሚገኙ ተቃዋሚ ሚዲያዎችና በቅርቡ ከተደረገው አመጽ ጋርም ግንኙነት አላቸው ሲል የኢራን የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ከሷል፡፡

ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ ከ 5ሺህ በላይ የሚሆኑ ሴት ተማሪዎች ተመርዘው መታመማቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃንና ባልሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ ፖለቲከኞች ምረዛው የተፈጸመው ትምህርትን በሚቃወሙ የሃይማኖት ቡድኖች ነው ሲሉ ይወነጅላሉ፡፡

አደገኛ መርዞችን ቀምመዋል የተባሉ ግለሰቦችን መያዙን ከነዚህ ውስጥም የተማሪ ወላጆችን እንደሚጨምር የአገር ውስጥ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ትናንት አስታውቋል፡፡

ተማሪዎቹ ደስ የማይል ሽታ ት/ቤት ውስጥ እንደሸተታቸውና ከዛም የትንፋሽ መቋረጥ፣ ማጥወልወል፣ ሽቅብ ማለትና ማዞር እንደገጠማቸው፣ አንዳንዶቹም በሆስፒታል ሕክምና እንደተሰጣቸው ተነግሯል፡፡

ሴት ተማሪዎችን መመረዝ “ይቅርታ የማይደረግለት” ተግባር መሆኑንና በሞት የሚያስቀጣም ተግባር ነው ሲሉ የአገሪቱ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ኮሚኒ ባለፈው ሰኞ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG