በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራን የኑክሌር አገልግሎት ዩራንየምን የማዳበር ሥራ መቀጠሉን አስታወቀ


የኢራን የኑክሌር አገልግሎት ከምድር በታች ባለው ፎርዶው የኑክሌር ተቋም ውስጥ ዩራንየምን የማዳበር ሥራ መቀጠሉን ዛሬ አስታውቋል።

ዩራንየም ኑክሌርን ለማንቀሳቀስ እንደ ነዳጅ ሆኖ የሚያገለግል ንጥረ ነገር ነው። ኢራን ከአራት ዓመታት በፊት ከኃያላን ሀገሮች ጋር ባደረግችው ሥምምነት መሰረት ዩራንየምን ላለማዳበርና ከማዳበር ጋር የተያያዘ ጥናትና ምርምር ላለማካሄድ ተስማምታ እንደነበር የሚታወቅ ነው።

ዩራንየምን የማበልፀጉ ሥራ የተጀመረው ትላንት ሌሊት መሆኑን አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኑክሌር ቁጥጥር አገልግሎት ባለሥልጣን እንደተመከቱት የኢራን የአቶሚክ ኤነርጂ ድርጅት ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል።

ዩራንየምን የምታዳብርበት ደረጃ እስከ 4.5 ከመቶ እንዲሆን ማቀድዋን ኢራን ገልፃለች። ከኃያላን ሀገሮቹ ባደረገችው ስምምነት መሰረት ከሚፈቀደው መጠን ትንሽ ከፍ ይላል።ኢራን ዩራንየሙን የመዳበሩ መጠን ከፍ ያደረገችው የኑክሌሩን ስምምነት የፈረሙት ሃገሮች በዩናይትድ ስቴትስ የተጣለባትን ማዕቀብ በመወጣት በኩል እንዲረድዋት ጥረት በምታደርግበት ወቅት ነው። ዩናይትድ ስቴትስ የጣለችባት ማዕቀብ ነዳጅ ዘይት ወደ ውጭ እንዳትልክ ይገድባታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG