ዋሺንግተን ዲሲ —
ቁልፍ ናቸው የተባሉ እነዚህ ስምምነቶች ሕንድ ቻባኻር የሚባለውን የኢራን ወደብ አገልግሎት ለመጭዎቹ 18 ወራት በኪራይ እንድትይዝ የሚፈቅዱን ውል እንደሚያካትቱ ተዘግቧል፡፡
ሕንድ ወደቡን የምታለማው ባላንጣዋን ፓኪስታንን ወደጎን በመተው የባሕር በር ለሌላቸው አፍጋኒስታንና ሌሎችም የማዕከላዊ እስያ ሃገሮች የንግድ መሥመር ለመክፈት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ስምምነቶች የተፈረሙት የኢራን ፕሬዚዳንት ሃሰን ሩሃኒ ሕንድን ለሦስት ቀናት እየጎበኙ ባሉበት ወቅት ነው፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ