በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን ከ30 ዓመት በፊት የፖለቲካ እስረኞችን መግደሏን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለፀ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል አዲስ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ መሠረት፣ ኢራን ከ30 ዓመታት በፊት ቢያንስ 5,000 የፖለቲካ እስረኞችን በድብቅ የገደለች በመሆኗ፣ በሰብዓዊ ፍጡራን ላይ ወንጀል ፈፅማለች። ይህንም የተመድ ሊመረምረው ይገባል ሲል ዓለማቀፉ የመብት ተከራካሪው ድርጅት አምነስቲ አሳስቧል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል አዲስ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ መሠረት፣ ኢራን ከ30 ዓመታት በፊት ቢያንስ 5,000 የፖለቲካ እስረኞችን በድብቅ የገደለች በመሆኗ፣ በሰብዓዊ ፍጡራን ላይ ወንጀል ፈፅማለች። ይህንም የተመድ ሊመረምረው ይገባል ሲል ዓለማቀፉ የመብት ተከራካሪው ድርጅት አምነስቲ አሳስቧል።

ኢራን በድብቅ የገደለቻቸው እነዚሁ የፖለቲካ እስረኞች፣ የተቃዋሚ ቡድን አባላትና ደጋፊዎች የነበሩ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸውም የት እንደደረሱ አያውቁም ብሏል አምነስቲ።

ኢራን የሰዎቹን መገደል ወይም መጥፋት እስከ ዛሬ አላመነችም።

“እነዚህ ሰዎች የት እንደደረሱ ወይም ምን እንደተፈጸመባቸው ኢራን እስካላመነች ድረስ፣ ወንጀሉ ትኩስ እንደሆነ ነው የሚቆጠረው” ሲሉ፣ የአምነስቲ ዋና ጸኃፊ ኩሚ ናዶ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG