በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የጠየቀው ኢራናዊ ሕይወቱን አጠፋ


የኢራን ካርታ
የኢራን ካርታ

አራት የፖለቲካ እስረኞች የማይፈቱ ከኾነ ራሱን እንደሚገድል በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ ያስታወቀው ኢራናዊ ጋዜጠኛና የመብት ተሟገች ሕይወቱ ማለፉን ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል።

የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ አገዛዝ ተቃዋሚና የቀድሞው የቪኦኤ ጋዜጠኛ ኪያኑሽ ሳንጃሪ ትላንት ረቡዕ ምሽት ላይ ነበር አራቱ የፖለቲካ እስረኞች የማይለቀቁና ይህንንም የፍትህ አካላት የማያስታውቁ ከሆነ ራሱን እንደሚያጠፋ ያስታወቀው።

ሳንጃሪ ነፍሱን በምን መንገድ እንዳጠፋ ግልጽ ባይሆንም፣ ትላንት ምሽት ከአንድ ሕንፃ ላይ ወደ ታች ሲመለከት የተነሳውን ፎቶ አጋርቶ ነበር።

“ማንም ሰው ሐሳቡን በመግለጹ ምክንያት መታሰረ የለበትም። ሕይወቴ ከዚህ መልዕክት በኋላ ሊያልፍ ይችላል። የምንሞተው ለሞት ካለን ፍቅር ሳይሆን ለሕይወት ካለን ፍቅር የተነሳ ነው” ሲልም ጽፏል።

በአንድ ወቅት ለአሜሪካ ድምጽ ይሠራ የነበረው ሳንጃሪ በእ.አ.አ 2015 ዕድሜያቸው የገፉ እናቱን ለመንከባከብ ወደ ሃገሩ ተመልሷል። በተደጋጋሚ ሲያዝና የፍርድ ቤት መጥሪያ ይደርሰው እንደነበርም የመብት ተሟጋቾች ይገልጻሉ።

ሳንጃሪ መሞቱ እንደተሰማ የሰብአዊ መብት ቡድኖች ሐዘናቸውን ገልፀዋል።

“የቀድሞ የቪኦኤ ጋዜጠኛና ሃገር ወዳዱ ኪያኑሽ ሳንጃሪ በኢራን አገዛዝ እስርና ጭቆና ምክንያት ለሞት በቅቷል።በመሞቱም ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶኛል” ሲሉ የቪኦኤ ዲሬክተር ማይክል አብራሞዊትዝ መልዕክታቸውን በ X ላይ አስፍረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG