በቅርቡ በመቐለ ከተማ ምክር ቤት ለከንቲባነት የተሾሙትና፣ ሹመታቸው በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ የታገደው የመቐለ ከተማ ምክር ቤት ዶ.ር ረዳኢ በርኸ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ የከተማዋ ምክር ቤት ወሰነ።
ምክር ቤቱ፣ ዛሬ ሐሙስ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ፣ በአወዛጋቢው የከተማዋ ከንቲባ ሹመት ላይ የተወያየ ሲኾን፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት እግዱን እንዲያነሱ ጠይቋል። ይህ ካልሆነ ግን የምክርቤቱ ውሳኔ እንዲተገበር ወስኗል።
የክልሉ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ የተሾሙት ከንቲባ ሕገወጥ ሥልጣን በመያዝ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ሥራ ያደናቅፋሉ ሲሉ፣ ከሹመቱ ማገዳቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል።
መድረክ / ፎረም