በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በየመን ከሚገኙ 200ሺሕ ፍልሰተኞች ከፊሉ ኢትዮጵያውያን እንደኾኑ አይኦኤም አስታወቀ


በየመን ከሚገኙ 200ሺሕ ፍልሰተኞች ከፊሉ ኢትዮጵያውያን እንደኾኑ አይኦኤም አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:58 0:00

በየመን ከሚገኙ 200ሺሕ ፍልሰተኞች ከፊሉ ኢትዮጵያውያን እንደኾኑ አይኦኤም አስታወቀ

ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት(IOM)፣ ሊጠናቀቅ በተቃረበው የአውሮፓውያኑ 2023፣ ከ6ሺሕ300 በላይ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ከየመን እንዳስመለሰ አስታወቀ፡፡

የተቋሙ የኢትዮጵያ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ባልደረባ አቶ ዓለማየሁ ሰይፈ ሥላሴ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ በአኹኑ ወቅት በየመን፣ ወደ 200 የሚደርሱና አብዛኞቹ ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የኾኑ ርዳታ የሚሹ ፍልሰተኞች እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

ከእነርሱም ውስጥ፣ ከ78 በመቶ በላይ የሚኾኑት ኢትዮጵያውያን እንደኾኑ፣ አቶ ዓለማየሁ ተናግረዋል፡፡

በአገሪቱ ያለው ጦርነት እና ግጭት፣ ይህንንም ተከትሎ የሚፈጠረው የሥራ ዐጥነት ችግር፣ ለዜጎች ፍልሰት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ውስጥ እንደኾኑ፣ አቶ ዓለማየሁ አክለው ገልጸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG