በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመን አፍሪካውያን ፍልሠተኞችን እያስወጣች ነው


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የመን አፍሪካውያን ፍልሠተኞችን በማስወጣት ላይ መሆንዋን ዓለምአቀፍ የፍልሠት ድርጅት/IOM/ ገለፀ፡፡

የየመን ባለሥልጣናት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድ ፍልሠተኞችን ወደ ጅቡቲ እያመለሱ መሆናቸውን የዓለምአቀፍ ፍልሰት ድርጅት/IOM/ አስታውቋል።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ኢታሊ ቪሪሪ በሰጡት ማብራሪያ ፍልሠተኞችን በግድ የሚያባርሩ መንግሥታትን አያግዝም ነገር ግን ዓለምአቀፍ የፍልሠት ድርጅት የሠብዓዊ በጎ አድራጎት ድርጅት እንደመሆኑ እንደ የመንን ከመሣሠሉ ሀገሮች በሚያሣቅቅ ሁኔታ ታፍሰው የሚባረሩ ሰዎችን አይቶ እንዳላየ ማለፍ እንደማይችል ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ፍልሠተኞች በምዕራባዊ የመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመሻገር የሚያደርጉት ጉዞ
ኢትዮጵያውያን ፍልሠተኞች በምዕራባዊ የመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመሻገር የሚያደርጉት ጉዞ

በቁጥር የሚበዙት ኢትዮጵያዋያን ያለ በቂ ምግብ፣ ውሃ እና የህክምና አገልግሎት በመኖር ላይ የነበሩ ፍልሠተኞች የመን እያስወጣች እንደምትገኝ ሲገልፁ፣ ባለፈው ሣምንት አንድ ጀልባ ላይ ታጭቀው የተላኩ ሠማኒያ ሁለት ኢትዮጵያዋያን ፍልሠተኞችን ከጅቡቲዋ ኦቦክ ከተማ ሠላሳ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ስፍራ ላይ እንዳሠፈሩዋቸውም ዓለምአቀፍ የፍልሠት ድርጅት/IOM/ ተጠሪ ተናገሩ ፡፡

ሊሳ ሽላይን ከዓለምአቀፍ የፍልሠት ድርጅት ዋና ጽህፈት ቤት ጄኔቫ ያስተላለፈቸውን ዘገባ ቆንጂት ታየ ታቀርበዋለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የመን አፍሪካውያን ፍልሠተኞችን እያስወጣች ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:13 0:00

XS
SM
MD
LG