በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በ2006 ተመቶ በወደቀው የማሌዥያ አውሮፕላን ምርመራ አበቃ፣ ስለፑቲን ፍንጭ እንጂ መረጃ አልተገኝም


ፎቶ ፋይል፦ የካቲት 10/2006 ዓ.ም ምስራቅ ዩክሬን ውስጥ በሩሲያ ሚሳዬል ተመቶ የወደቀው የማሌዥያ መንገደኞች አውሮፕላን
ፎቶ ፋይል፦ የካቲት 10/2006 ዓ.ም ምስራቅ ዩክሬን ውስጥ በሩሲያ ሚሳዬል ተመቶ የወደቀው የማሌዥያ መንገደኞች አውሮፕላን

የዓለም አቀፍ መርማሪዎች፣ የካቲት 10/2006 ዓ.ም ምስራቅ ዩክሬን ውስጥ በሩሲያ ሚሳዬል ተመቶ የወደቀው የማሌዥያ መንገደኞች አውሮፕላን ጉዳይ ላይ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እጅ ያለበት ስለመሆኑ “ጠንካራ ፍንጮች” ቢኖሩም እርሳቸውና ሌሎቹ ባለሥልጣናት ላይ የወንጀል ክስ ለመመስረት የሚያበቃ የተጨበጠ መረጃ አለመኖሩን በመግለጽ ምርመራውን ያበቃ መሆኑን አስታውቋል፡፡

298 የሚደርሱ መንገደኞችና የበረራ ሠራተኞች ከሞቱበት የሲቪል አውሮፕላን ጋር ሩሲያ ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላት መሆኑን አስተባብላለች፡፡

ባላፈው ህዳር የሆላንድ ፍርድ ቤት በሁለት የቀድሞ የሩሲያ መረጃ ሠራተኞች እና የዩክሬን ተገንጣይ አባላት መሪ፣ ሰዎችን በመግደልና አውሮፕላኖችን መትተው የሚጥሉ የሩሲያ ሚሳዬሎችን በማቀናጀት ረድተዋል በሚል ጥፋተኛ አድርጓቸዋል፡፡

ሦስቱም ግለሰቦች ጥፋተኞች የተባሉት በሌሉበት ሲሆን አሁንም ያልተያዙ መሆኑን ተዘግቧል፡፡

አውሮፕላኑ ተመቶ የወደቀው በሩሲያ የሚደገፉ የዩክሬን ተገንጣይ ኃይሎች ከዩክሬን ጦር ጋር በምስራቅ ዩክሬን ዶኔትስክ ግዛት ይዋጉ እንደነበር ተነግሯል፡፡

ሩሲያ መጋቢት 2006 ዓ.ም ክሬሚያን ከዩክሬን በመገንጠል ከራሷ ግዛት ጋር የቀላቀለችበት ጊዜ ቢሆንም፣ በወቅቱ በዶኔትስክ ግዛት በነበረው ውጊያ ተካፋይ አለመሆንዋን ገልጻለች፡፡

XS
SM
MD
LG