በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሕይወት ለማዳን የዋለ ጥበብ እና አሳቢነት


Faruk Mubarek, Aircraft Engine Technician, Ethiopian Airlines, 3D artist
Faruk Mubarek, Aircraft Engine Technician, Ethiopian Airlines, 3D artist

ክፍል ሁለት

"ማሰብ የቻልነውን ያህል" መስራት የሚቻልበት የመጪው ዘመን ቴክኖሎጂ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:50 0:00

ከጊዜያችን ብርቱ ፈተናዎች አንዱ ለሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ የሚውሉ ሁነኛ መላ ፍለጋ የሚደረገው ጥረት በሁሉም አቅጣጫ ቀጥሏል።

በዚህ መላውን የሰው ልጆች በገጠመ ፈተና እንደየተሰማሩበት ሞያና እንደየክህሎቶቻቸው የተያዘው ጥረት አጋዥ ለመሆን የበኩላቸውን ለማድረግ ደፋ ቀና የሚሉት ብዙዎች ናቸው።

የወረርሽኙን የጥድፊያ መዛመት ለመግታትት ሁነኛ የመከላከያ ብልሃቶችን በመቀየስ አገራዊውን ጥረት ከሚያጎለብቱት፤ ከፍተኛ እጥረት የሚታይባቸውን አስፈላጊ ቁሳቁሶች እጥረት ለመቀነስ የሚያግዙ መላዎችን እስከሚፈነጥቁት ይዘልቃሉ።

የኮቪድ 19 ህሙማንን ለመርዳት በግንባር የተሰለፉትየሕክምና ባለሞያዎች ለበሽታው እንዳይጋለጡ ለማድረግ በታለመ ጥረት '3D ፕሪንተር' በመባል የሚታወቀውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ የመከላከያ ቁሳቁሶችን በመስራት ላይ የሚገኝ ወጣት ነው።

ፋሩቅ ሙባረክ ይባላል። ስለ ስራውና ለዚህ መልካም ዓላማ ያነሳሱትን ምክኒያቶች ጨምሮ ሊያጫውተን ከአዲስ አበባ በስልኩ መስመር ብቅ ብሏል። የቃለ ምልልሳችንን ተከታታይ ክፍሎች ከዚህ ያድምጡ።

ክፍል አንድ

ሕይወት ለማዳን የዋለ ጥበብ እና አሳቢነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:50 0:00


XS
SM
MD
LG