በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶስት የኒውክሌር ተመራማሪዎች የ2023 የፊዚክስ የኖቤል ተሸላሚ ሆኑ

የስዊድን ሮያል የሳይንስ አካዳሚ ፒየር አጎስቲኒ’ን፣ ፌሬንች ክራውስዝ’ን እና አን ልዊሊየ “በአተሞች እና ሞለኪውሎች ውስጥ ያሉ ኤሌክትሮኖችን በማጥናት” ያደረጓቸውን ሳይንሳዊ ሙከራዎች በመጥቀስ ሶስቱ የኒዩክሌር ተመራማሪ ሳይንቲስቶች በፊዝክስ የዓመቱ የኖቤል ተሸላሚ መሆናቸውን በሮያል ስዊድን የሳይንስ አካዳሚ ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ተደረገ ስቶክሆልም፣ ስዊድን፣ እአአ ጥቅምት 3/2023

የስዊድን ሮያል የሳይንስ አካዳሚ ፒየር አጎስቲኒ’ን፣ ፌሬንች ክራውስዝ’ን እና አን ልዊሊየ “በአተሞች እና ሞለኪውሎች ውስጥ ያሉ ኤሌክትሮኖችን በማጥናት” ያደረጓቸውን ሳይንሳዊ ሙከራዎች በመጥቀስ ነው ሶስቱ የኒዩክሌር ተመራማሪ ሳይንቲስቶች በፊዝክስ የዓመቱ የኖቤል ተሸላሚ መሆናቸውን ይፋ ያደረገው።

አካዳሚው አክሎም፣ ሦስቱ ተመራማሪዎች “ኤሌክትሮኖች የሚንቀሳቀሱበትን ወይም ኃይልን የሚቀይሩባቸውን ፈጣን ሂደቶች ለመለካት የሚያገለግሉ እጅግ በጣም አጭር የብርሃን ምቶች የሚፈጠ’ሩበትን መንገድ አሳይተዋል” ብሏል።

የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከፈረንሳይ ዩኒቨርሲቲ የተቀበሉት አጎስቲኒ፣ በዩናይትድ ስቴትሱ የኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ኢሜሪተስ ፕሮፌሰር ሲሆኑ፤ የሃንጋሪ ተወላጅ የሆኑት ክራውስዝ በጀርመኑ ማክስ ፕላንክ የኳንተም ኦፕቲክስ የምርምር ተቋም ያገለግላሉ። የፈረንሳይ ተወላጇ ልዊሊየ በበኩላቸው በስዊድኑ ለንድ ዩኒቨርቲ መምሕር ናቸው።

የኖቤል ሽልማት የሚያስገኘውን የሞያ እውቅና እና የ1 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ሽልማት ይጋራሉ። በተያያዘም ልዊሊየ በፊዚክስ የኖቤል ሽልማት ያገኘች አምስተኛዋ ሴት ተመራማሪ ሆነዋል።

በትላንትናው ዕለት ይፋ መደረግ የጀመረው የዘንድሮው የኖቤል ሽልማት በሕክምና ሳይንስ ዘርፍ ሃንጋሪያዊው ካታሊን ካሪኮ እና አሜሪካዊው ድሩ ዋይስማን ለኤምአርኤንኤ የኮቪድ ክትባት በፍጥነት መገኘት ለረዳው የምርምር ስራቸው በጋራ አሸናፊ ሆነዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG