ዋሺንግተን ዲሲ —
“ዕጣ ፈንታቸው የዚህ ስደት አካል ለመሆን ለተገደዱና ከቦታ ቦታ በመንከራተት ላይ ለሚገኙ ቁጥራቸው በሚሊዮኖች የሚደርስ ሕፃናት ደኅንነትና ጥበቃ መረጋገጥ ሀገሮች ይበልጥ መትጋት አለባቸው” ሲል የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት፣ ዩኒሴፍ በዛሬው ዕለት ባሰማው ጥሪ አሳስቧል።
ሃምሳ ሚልዮን ሕፃናት ዛሬ በዓለም ዙሪያ ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው፤ ያለው ዩኒሴፍ “የተሻለ ሕይወት” ፍለጋ በፈቃዳቸው በስደት ወደተለያዩ አካባቢዎች በማቅናት ላይ ካሉ ወላጆቻቸው ጋር በሚያደርጉት ጉዞ ከሞላ ጎደል ደኅንነታቸው የተጠበቀ ሕፃናት ቢኖሩም፤ ሌሎች አያሌ ሚልዮን ሕፃናት ግን ጉዞ በፈቃዳቸው የሚደረግ ደኅንነታቸውም ከእንግልትና ከአደጋ የራቀ አይደለም፤ ብለዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ