በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ለመንግሥታቱ ድርጅት ጥያቄ ቀረበ


የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት /የሎጎ ሥዕል ከፋይል የተገኘ/
የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት /የሎጎ ሥዕል ከፋይል የተገኘ/

የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ መርማሪዎችን ሃሣብ እንደማይቀበል በድጋሚ አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ለመንግሥታቱ ድርጅት ጥያቄ ቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:46 0:00

የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎቹ በኦሮምያና በአማራ ክልሎችና በሌሎችም አካባቢዎች የሚወስዷቸውን ከመጠን ያለፉና አስፈላጊ ያልሆኑ እስከ ግድያ የሚደርሱ እርምጃዎቻቸውን በአስቸኳይ እንዲያቆስቆም ጥሪ እንዲተላለፍለት የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች የሆኑ ተቋማትና ቡድኖች ጠየቁ፡፡

አሥራ አምስት ዓለምአቀፍ ድርጅቶችና ተቋማት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ባስገቡት ደብዳቤአቸው ካሰፈሯቸው ስድስት ጥያቄዎች መካከል መንግሥቱ በተቃውሞዎቹ ወቅትና ከዚያም በኋላ በዘፈቀደ ያሠራቸውን ጋዜጠኞች፣ የሰብዓው መብቶች ተሟጋቾች፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎችና አባላት፣ እንዲሁም በሰልፎች ላይ የተሣተፉትን ያለድርድርና በአፋጣኝ እንዲፈታ ምክር ቤቱ የኢትዮጵያን መንግሥት እንዲጠይቅ አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዩ ምርመራ ቡድኖች ወደ ሃገሪቱ እንዲገቡ ለቀረቡለት ጥያቄዎች መንግሥቱ አዎንታዊ መልስ እንዲሰጥ፣ እንዲሁም ዓለምአቀፍ የሆነ ጥልቀት ያለው ነፃና ከወገንተኝነት የፀዳ ግልፅ ምርመራ እንዲካሄድ ፈራሚዎቹ ድርጅቶች አሳስበዋል፡፡

በሃገሪቱ ውስጥ ለተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎች ተጠያቂ ናቸው የሚባሉ ዓለምአቀፍ ሕግጋትንና ደረጃዎችን በጠበቀ ሁኔታ እንዲጠየቁና በነፃ ፍትሕ እንዲዳኙ ማረጋገጫ እንዲሰጥ የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎች ለመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ዛሬ ያስገቡት ድርጅቶች ጠይቀዋል፡፡

ደብዳቤውን የፈረሙት አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የሚሟገቱ ማኅበር፣ ሲቪከስ በሚል ምኅፃር የሚጠራው የዓለም የዜጎች ተሣትፎ ጥምረት፣ የሲቪል መብቶች ዘቦች፣ እንዲሁም ለዘቦች ዘብ ቁሙ የሚባለው ተቋም የምሥራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ፕሮጀክት፣ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት፣ የሰብዓዊ መብቶች ዓለምአቀፍ ፌደሬሽን፣ የሰብዓዊ መብቶች ተነሣሽነት ድርጅት፣ ፍሪደም ሃውስ፣ የግንባር መስመር ተከላካዮች፣ የደኅንነት ጥበቃ ኃላፊነት ዓለምአቀፍ ደኅንነት፣ ሂዩማን ራይትስ ዋች፣ የሰብዓዊ መብቶች ዓለምአቀፍ አገልግሎት፣ ድንበር የለሽ ሪፖርተሮች፣ የስቃይ አያያዝ ተቃዋሚ ዓለምአቀፍ ድርጅት ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤቱ አባልና ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆኗ የሰብዓዊ መብቶችን ጥበቃ ከፍተኛ ደረጃ ልታሟላ የሚጠገባት ሃገር መሆኗን የሚያስታውሰው ይህ ጥያቄ በመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ውሣኔ 60/251፣ ኦፒ 9 መሠረት ሙሉ በሙሉ መተባበር እንደሚኖርባት ያሳስባል፡፡

ደብዳቤው በሃገሪቱ ውስጥ ተፈፅመዋል የሚላቸውን ግድያዎችና እሥራቶችም ቦታና ሁኔታ ይናገራል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ በተቃውሞዎች ወቅት ተፈፀሙ የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን መንግሥቱ ሙሉ በሙሉ እንዲያጣራ ወይም ለአህጉራዊና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ያልተገደበ የማጣራት ፈቃድ እንዲሰጥ የአፍሪካ የሰብዓዊና የሕዝቦች መብቶች ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል።

በነዚሁ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችና ግጭቶች ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው የተሟላ ካሣና ማቋቋሚያ ማግኘታቸውን እንዲያረጋግጥም ኮሚሽኑ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በሰጠው ምላሽ አህጉራዊም ሆነ ዓለምአቀፍ ቡድኖች እንደማይጋበዙ አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG