በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደማስቆ አየር ማረፊያ ተቋርጦ የከረመው ዓለም አቀፍ በረራ ቀጠለ


ተጓዦች ደማስቆ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፤ እአአ ጥር 7/2024
ተጓዦች ደማስቆ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፤ እአአ ጥር 7/2024

የሶሪያ እስላማዊ አማፂያን ባለፈው ወር ላይ የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት በሽር አል አላሳድን ከሥልጣን ካስወገዱ በኋላ፤ በዋናው የደማስቆ አውሮፕላን ማረፊያ ተቋርጠው የቆዩት ዓለም አቀፍ በረራዎች ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ መቀጠላቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

በአውሮፕላን ጣቢያው ከካታር የተጓዙ መንገደኞች ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል፡፡ የአየር ማረፊያው ዳይሬክተር አኒስ ፋላህ “ዛሬ አዲስ ምዕራፍ የተመዘገበበት ቀን ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አያይዘውም

"ወጪ እና ገቢ ዓለም አቀፍ በረራዎችን መቀበል ጀምረናል" በማለት የመጀመሪያው በረራ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሻርጃ መጓዙን ጠቁመዋል፡፡

የካታሩ የመንገደኞች አውሮፕላን ከ13 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ደማስቆ አውሮፕላን ጣቢያ አርፏል፡፡

ወደ ሻርጃ ያቀናው የሶሪያ አየር መንገድ በረራ ዕኩለ ቀን ገደማ ላይ የተነሳ ሲሆን ከጎርጎርሳውያኑ ታሕሳስ ስምንት በኋላ ከአውሮፕላን ማረፊያው የተነሳ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የንግድ አውሮፕላን በረራ መሆኑን የአሶሺየትድ ፕሬስ ዘጋቢዎች ተናግረዋል።

ለረጅም ጊዜ የዘለቀው ጸረ አሳድ ተቃውሞ ምልክት ሆኖ የሚታየው እና አዲሶቹ ባለስልጣናት የተቀበሉት ባለ ሦስት ኮከቡ የሶርያ ነጻነት ባንዲራ አውሮፕላኑ ላይ በአርማነት ተስሏል፡፡

ዓለም አቀፍ የረድዔት ማጓጓዣ እና የውጭ ሀገር ዲፕሎማቶችን የያዙ ሶሪያ ሲያርፉ የቆዩ ሲሆን የአገር ውስጥ በረራዎችም ጀምረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG