አዲስ አበባ —
ማንኛውም ክፍል ከምንም ነገር በላይ ለሰው ህይዎት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሳሰበ።
ጉባኤው በሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባወጣው የአቋም መግልጫ፣ ከሁሉም በላይ ሃላፊነት ያለበት መንግስት በመሆኑ በአርቆ አስተዋይነትና በአባታዊ መንፈስ ተገቢውን ሁሉ እንዲያደርግ ጠይቋል።
ህዝቡም ከጥላቻ፣ ከአድማና ከሁከት እንዲርቅና ጥያቄውን በሰላማዊ መንድ እንዲያቀርብ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡