በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ “ውይይትና ይቅርታ” እንዲቀድሙ ጠየቀ


የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ “ውይይትና ይቅርታ” እንዲቀድሙ ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:49 0:00

የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ “ውይይትና ይቅርታ” እንዲቀድሙ ጠየቀ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች የተፈጠረውን ችግር ስፋትና ጥልቀት ተገንዝበው ውይይትን፣ ይቅርታንና እርምትን እንዲያስቀድሙ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠየቀ።

የችግሩ መባባስ በጽኑ እንዳሳሰበው የገለጸው ጉባዔው የፌዴራልና የክልሎች መንግሥታት በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የተፈጠረው ችግር በራሷ በቤተክርስቲያኒቱ ሕግ፣ ቀኖናና ሥርዓት ብቻ ተመሥርቶ እንዲፈታ ኃላፊነታቻውን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 11 እና 27 መሠረት እንዲወጡ አሳስቧል።

በሌላ በኩል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት የቤተክርስቲያኗን ወቅታዊ ጉዳይ በማስመልከት ትላንት ያወጣውን መግለጫ እንደማትቀበል ቤተክርስቲያኗ በሰጠችው ምላሽ አስታውቃለች፡፡

ቤተክርስቲያን ያቀረበችውን ጥሪ ተከትሎ ቁጥራቸው የበዛ ምዕመናን ዛሬ ጥቁር አልባሳትን ለብሰው ታይተዋል፡፡

ቤተክርስቲያኗ ጥያቄዋ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ ለየካቲት 5/2015 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ የጠራች ሲሆን “የኦሮሚያ እና የብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ” በሚል በተገንጣይ ቡድኖች መቋቋሙ የተገለጸው አካልም፣ በተመሳሳይ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ለአንድ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG