በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የታሠሩ ዐስራ ስድስት ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ሲፒጄ ጠየቀ


የታሰሩ ጋዜጠኞች ቤተሰቦችን አነጋግረናል።

ዋና መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋቹ ሲፒጄ በመላው ዓለም በእስር ላይ ከሚገኙ 259 ጋዜጠኞች ውስጥ ዐስራ ስድስቱ በኢትዮጵያ የታሠሩ እንደሆኑ ገልጾ እስረኞቹ በእስር ቤት ሊያገኙት የሚገባውን መብት ተነፍገዋል ብሏል።

የታሰሩት ጋዜጠኞች ቤተሰቦች እስረኞቹን በበቂ ሁኔታ መጎብኘት እንደማይፈቀድላቸው ገልፀው አንዳንዶቹ በአንድ ሰው ያውም ለጥቂት ደቂቃ ብቻ እንደሚጎበኙ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ እንደ ሲፒጄ ያሉ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት የሚያወጡትን ሪፖርት አይቀበልም በጋዜጠኝነት ሞያው የታሰረ ጋዜጠኛ የለም ሲልም ይከራከራል።

ጽዮን ግርማ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

በኢትዮጵያ የታሠሩ ዐስራ ስድስት ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ሲፒጄ ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:34 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG