በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦስት የደቡባዊ አፍጋኒስታን ከፍተኛ ባለሥልጣኖች በተኩስ ልውውጥ ተገደሉ

የፖሊስ አዛዥ ጄነራል አብዱል ራዚክ
የፖሊስ አዛዥ ጄነራል አብዱል ራዚክ

አፍጋኒስታን ውስጥ ኃያሉ የፖሊስ አዛዥ ጄነራል አብዱል ራዚክ የሚገኙባቸው ሦስት የደቡባዊ አፍጋኒስታን ከፍተኛ ባለሥልጣኖች በተኩስ ልውውጥ ወቅት ተገድለዋል። ይህ የሆነው ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ጄኔራል ክፍለ ሀገሪቱን ይጎበኙ በነበረበት ወቅት ነው።

አፍጋኒስታን ውስጥ ኃያሉ የፖሊስ አዛዥ ጄነራል አብዱል ራዚክ የሚገኙባቸው ሦስት የደቡባዊ አፍጋኒስታን ከፍተኛ ባለሥልጣኖች በተኩስ ልውውጥ ወቅት ተገድለዋል። ይህ የሆነው ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ጄኔራል ክፍለ ሀገሪቱን ይጎበኙ በነበረበት ወቅት ነው።

አሜሪካዊው ጄኔራል ስካት ሚለር ከካንደሀር አስተዳዳሪና ከሌሎች የክፍለ ሀገሩ ባለሥልጣኖች ጋር ለመነጋገር በአስተዳዳሪው ቅጥር ጊቢ ውስጥ ነበሩ። ጉዳት አልደረሰባቸውም። የአከባቢው ሚድያ በገለጸው መሰረት ባለስልታኖቹ ከተነጋገሩ በኋላ ወደ ሄሊፓድ ባመሩበት ወቅት ነው ተኩሱ የተከፈተው።

ሪዛክ ከታሊባን ከተሰነዘሩባቸው በርካታ የመግደል ሙከራዎች ተርፈው ነበር። ከሳቸው ሌላ የክፍለ ሀገሩ አስተዳዳሪና የሥለላ አገልግሎት ኃላፊ ዛሬ በተከፈተባቸው ጥቃት ተገድለዋል። ሁለት አሜሪካውያን ወታደሮች በጥቃቱ ቆስለዋል። አንድ የአከባቢው ፎቶግራፍ አንሺ ህይወቱ አልፏል።

ታሊባን ዛሬ ለጥቃቱ ኃላፊነት በመውስድ የጥቃቱ ዒላማዎች ጄኔራል ራዚክና አሜሪካዊው ጄኔራል እንደነበሩ ገልጿል። ጥቃቱን ያካሄዱት ሰርጎ ገቦች ናቸው ብሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG