በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኔስሊ ኩባኒያ የህፃናት ወተት ከውጭ ሊያስመጣ ነው


ታርጌት ሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ አንዲት ሴት የሕፃን ፎርሙላ ለመግዛት ፍለጋ ሲያካሄዱ በአናፖሊስ፣ ሜሪላንድ እአአ ግንቦት 16/2022
ታርጌት ሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ አንዲት ሴት የሕፃን ፎርሙላ ለመግዛት ፍለጋ ሲያካሄዱ በአናፖሊስ፣ ሜሪላንድ እአአ ግንቦት 16/2022

ግዙፉ የስዊሱ ምግብ አምራች ኩባኒያ ኒስሊ የህፃናት ወተት እጥረት ችግር ላይ ወደምትገኘው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ከስዊትዘርላንድ እና ከኔዘርላንድስ በአውሮፕላን ሊያስገባ መሆኑን አስታወቀ።

እጥረት የላም ወተት ፕሮቲን የማይስማማቸውን ህፃናት ወላጆች ተጨማሪ ጭንቀት በመፍጠሩ ቅድሚያ ሰጥተን ለነሱ የሚሆን ወይም ሁለት ዓይነት ወተት እናስመጣለን ሲሉ የኩባኒያው ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

ለህፃናቱ ጤና የግድ አስፈላጊ በመሆኑ ቅድሚያ እንሰጣለን ብለዋል። ፊቱንም ሁለቱ የህፃናት ወተት ዓይነቶች ከውጭ የሚገቡ ሲሆኑ ገርበር ጉድ ስታርት የተባለው ከኔዘርላንድስ አልፋሚኖ ወተት ደግሞ ከስዊትዘርላንድ የሚገቡ መሆኑ ተገልጿል። ኔስሊ አቅርቦቶቹን ከአውሮፓ በአውሮፕላን አስጭኖ የሚያስገባው ላለው ዕጥረት ፈጥኖ ለማድረስ መሆኑን አመልክቷል።

የስዊሱ ኩባኒያ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሁለት የህፃናት ወተት አምራች ፋብሪካዎች አሉት። የህጻናት ወተት /ፎርሙላ/ እጥረቱ መጀመሪያ ላይ የተፈጠረው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ በተከሰተው የአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል የተነሳ ሲሆን በኋላ ደግሞ በየካቲት ወር "አበት" ፋብሪካ ለሁለት ህፃናት ሞት ምክንያት ተደርገው የተጠረጠሩትን ምርቶቹን አስመልሶ ሚሺጋን ውስጥ ያለው ፋብሪካው መዘጋቱን ተከትሎ ዕጥረት ተባብሷል።

የዩናይትድ ስቴትስ የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር ፋብሪካው ወተቱን ማቅረብ እንዲጀምር ፈቅዶ ፋብሪካው ችግሮች እንዳሉበት የሚያመለክት ቅጽ ማያያዙን የገለጸው አበት ወዲያውኑ የእርምት እርምጃዎች መውሰድ ጀምረናል ብሏል። "አበት" በፋብሪካው የምርት ስራውን ለመጀመር ባለፈው ሰኞ ከዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ሥምምነት ላይ ደርሷል።

ዋይት ኃውስ ምርት ከፍ እንዳይል የሚከለክሉ የማጓጓዣ፣ የሎጂስቲክስ እና የአቅራቢ ዘርፎች ችግሮችን ለመለየት ከዋና ዋናዎቹ አምራች ኩባኒያዎች ከኔስሊ፣ ሪኪት፣ አበት እና ፐሪጎ ጋር በተከታታይ እየተነጋገረ ነው።

XS
SM
MD
LG