የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር ጂም ማቲስ ሀገራቸው ከኢንዶኔዥያ ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብር ለማሳደግ ያላቸውን ዕቅድ አስታወቁ። ምን ዓይነት የትብብር ሥራዎችን መሥራት እንደሚችሉ የተሻለ ሃሳብ ያላቸው መሆኑን ተናገሩ።
በሌላ በኩል የኢንዶኔዥያ ልዩ ኃይል፤ በአሁኑ ወቅት ለሥራ ጉብኝት ከዚያ ለሚገኙት የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር ጂም ማቲስ የተቀነባበረ የፀረ ሽብር መልሶ ማጥቃት ትርዒት አሳይቷል።
ከወገባቸው በላይ እርቃናቸውን የሆኑና ፊታቸውን ወታደራዊ ዘመቻ አመላካች ቀለም የተቀቡ፥ ፈርጣማ ክንድ ያላቸው ወታደሮች በሚንቀለቀል እሳት የተሸፈነ የጡብ ክምር በጭንቅላታቸው በመፈረካከስ አሳይተዋል። የኮማንዶ ቡድኑ አባላት በተጨማሪም የእባብ ጭንቅላት በጥርሳቸው እየቀነጠሱ ደሙን በመጠጣት ልዩ ትዕይንት አመልክተዋል።
ሦሥት መካከለኛ እና ገዘፍ ያለ መጠን ያላቸው የሰለጠኑ ውሾች ከሄሊኮፕተር ተጥለው በአሸባሪዎች የታገቱ ሠዎችን የማስለቀቅ ሥራ ሲሰሩ፤ በዝነኛው 'Mission Impossible'/አይሞከሬ/ የተሰኘው የሥለላ ታሪክ የተላበሰ ፊልም የሚታወቅ ሙዚቃ ይጫወታል።
በኢንዶኔዥያው የጦር ሠራዊቱ ዋና ጽ/ቤት ቅጥር ጊቢ የተካሄደውን ወታደራዊ ትርዒት ከሀገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን ለሃያ ደቂቃዎች ያህል የተመለከቱት ማቲስ በተመለከቱት መመሰጣቸውን ተናግረዋል።
ማቲስ ከትርዒቱ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት “ይህን መሰል በርካታ ጥቃቅን ነገሮች እጅግ በተዋጣለት መንገድ የሚሠራ ኃይል ስትመለከት፤ ግዙፎቹን ጉዳዮች በወጉ ማሳካት የሚችል ኃይል መሆኑን መረዳት አያዳግትም” ሲሉ
አድናቆታቸውን ገልፀዋል።
“ከሄሊኮፕተር የወረዱት ውሾች እንኳን የሚሠሩትን የሚያውቁ ናቸው” ሲሉ የቀለዱት የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር “ትልልቆቹን አስፈላጊ ጉዳዮች”ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ