ዋሺንግተን ዲሲ —
የኢንዶኔዥያ ፀረ-ሙስና መሥሪያ ቤት የሀገሪቱ ፓርላማ አፈ-ጉባዔ፣ የ$170 ሚሊዮን ስጦታ ተቀብለዋል በሚል፣ በቁጥጥጥ ሥር አዋላቸው። ሲትዮ ኖቫንቶ ትናንት ማታ ነው ወደ ወህኒ የተላኩት።
አንድ የፀረ ሙስና መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ እንደገለፀው፣ አፈ-ጉባዔ ኖቫንቶ፣ ጥያቄ እየቀረበለው ለ20 ቀን በእሥር ይቆያሉ።
አፈ-ጉባዔው በሰጡት ቃል ግን፣ ምንም ጥፋት እንዳልፈፀሙ ነው የተናገሩት።
ባለሥልጣናት በበኩላቸው፣ ኖቫስቶ የመንግሥት ገንዘብ የመነተፉት፣ አዲስ የመታወቂያ ወረቅት ለማዘጋጀት ከተሰየመው ቡድን መካከል ሆነው በሚሠሩበት ጊዜ መሆኑን አመልክተዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ