በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢንዶኒዥያ ጃቫ ባህር ላይ ከተከሰከሰው አውሮፕላን ጥቁር ሳጥኖች አንዱ ተገኘ


የኢንዶኒዥያ የባህር ሃይል ጠላቂዎች በጃቫ ባህር ላይ ከተከሰከው /JT-610/ የላየን አየር መንገድ በረራ አውሮፕላን “ጥቁር ሳጥኖች” አንዱን ማግኘታቸውን ገልፀዋል። ጄት አይሮፕላኑ ከጃካርታ እንደተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ነው የተከሰከሰው።

የኢንዶኒዥያ የባህር ሃይል ጠላቂዎች በጃቫ ባህር ላይ ከተከሰከው /JT-610/ የላየን አየር መንገድ በረራ አይሮፕላን “ጥቁር ሳጥኖች” አንዱን ማግኘታቸውን ገልፀዋል። ጄት አውሮፕላኑ ከጃካርታ እንደተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ነው የተከሰከሰው።

ጠላቂዎቹ ዛሬ ለቴሌቪዥን ጣብያ ዘጋቢዎች በተናገሩት መሰረት አንደኛውን የአውሮፕላኑን የቀረፃ መሳርያን ያገኙት በባህር ወለል ላይ ነው።

የፍለጋ ሰራተኞችቹ ቦይንግ 737 ማክስ 8 የተባለው ጄት አይሮፕላን ስብርባሪዎችን ለመግኘት ቀንና ሌሊት ሲሰሩ ሰንብተዋል። ጥቁር ሳጥን በአይሮፕላኖች በረራ ወቅት ሂደቶቹን ሁሉ የሚመዘግብ መሳርያ በመሆኑ ስለበረራውና አይሮፕላን አብራሪው በየብስ ከነበሩት ተቆጣጣሪዎች ጋር ስለተነጋገረው ነገር ወሳኝ መረጃ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። አብራሪው ወደ አውሮፕላን ማረፍያው ለመመለስ ጠይቆ እንደነበር ተዘግቧል።

ባለሥልጣኖች የላየን አየር መንገድ ጄት አውሮፕላኑ የወደቀበትን ቦታ ለይተናል ብለው እንደሚያምኑ ትላንት ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG