በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢንዲኒዥያ በደረሰው ከባድ ርዕደ መሬትና ሱናሚ ከ1 ሺህ 2መቶ በላይ ሰዎች አልቀዋል

ባለፈው ሳምንት ኢንዲኒዥያ ላይ በደረሰው ከባድ ርዕደ መሬትና ሱናሚ ምክንያት ሲላዌዚ በተባለው የሀገሪቱ ማዕከላዊ ደሴት ላይ ቀቢፀ ተስፋነት እየተንፀባረቀ ነው። እስካሁን ባለው ጊዜ ከ1 ሺህ 2መቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎች አልቀዋል።

ባለፈው ሳምንት ኢንዲኒዥያ ላይ በደረሰው ከባድ ርዕደ መሬትና ሱናሚ ምክንያት ሲላዌዚ በተባለው የሀገሪቱ ማዕከላዊ ደሴት ላይ ቀቢፀ ተስፋነት እየተንፀባረቀ ነው። እስካሁን ባለው ጊዜ ከ1 ሺህ 2መቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎች አልቀዋል።

በቀውሱ ክፉኛ የተጎዳችው ፓሉ ከተማ ነዋሪዎች፣ ሰዎች ምግብና ንፁህ የመጠጥ ውሃ ፍልጋ ጠባቂ የሌላቸው ሱቆችን እየዘረፉ መሆናቸውን ገጸዋል። መንግሥት በአስቸዃይ አቅርቦታ ላይ አልፈጠነም በማለት ነዋሪዎቹ እየተቆጥ ናቸው።

በሌላ በኩል ደግሞ በህይወት የተረፉ ሰዎች ካሉ ለማዳን ሲሉ የመድኅን ሰራተኞች በፓሉ ከተማ ዙርያ በተበታተነው ስብርባሪ እየፈለጉ ናቸው። ቢያንስ 50 ሰዎች “ሮአ ሮአ “ከተባለው ሆቴል ሥር መውጫ አጥተዋል ተብሎ ይታመናል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG