ዋሺንግተን ዲሲ —
ኢንዶኔዥያ ውስጥ ሰሞኑን የተነሣ ሱናሚ ጉዳት ባደረሰባት የጃቫ ግዛት ምዕራባዊ የባሕር ዳርቻ ሰዉ አሁንም ሌላ አደጋ ሊደርስ ይችላል በሚል ሥጋት በአብዛኛው አካባቢውን ለቅቆ መውጣቱ ተዘገበ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የከትናንት በስተያው ቅዳሜ በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ሰዎች አማኒያን ምኅላና ፀሎት እንዲያደርሱ እዚያው የሚገኙ የአብያተ-ክርስትያን አባቶች ጥሪ እያሰሙ ናቸው።
የዛሬው የገና በዓልም በአብያተ-ክርስትያኑና በሰምዕመናኑ ዘንድ እየተከበረ ያለው በኀዘንና በትካዜ መንፈስ መሆኑ ተገልጿል።
የተነሣው በአቅራቢያው በሚገኝ ተራራ ላይ የፈነዳው እሣተ-ገሞራና ተያይዞም በባሕር ውስጥ በተፈጠረ የመሬት መናድ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም በተባለው ሦስት ክፍላተ-ሃገር ባዳረሰው ድንገተኛ ማዕበል የሞተው ሰው ቁጥር እስከአሁን 429 መድረሱን የኢንዶኔዥያ የአደጋ ሥራ አመራር ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ